ለመስኖ የሚለሙ የተሻሻሉ ዝርያዎች


እስካሁን ድረስ በተካሄደው የስንዴ ዝርያዎች ድቀላና መረጣ  ሥራዎች በቂ ዝናብ ላላቸው ደጋና ወይና ደጋ አካባቢዎች እንዲሁም ዝናብ አጠር አካባቢዎች በርካታ የዳቦና የፓስታ,ማኮሮኒ ስንዴ ዝርያዎች ተለቀው ወደ ምርት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በመስኖ ለሚለሙ ወይና ደጋና ቆላማ የሀገራችን አካባቢዎች የፓስታ-ማኮሮኒ እና የዳቦ ዝርያዎች በወረርና ቁልምሳ ግብርና ምርምር ማዕከላት በመስኖ በመልማት ላይ የሚገኙ ዝርያዎችን ከነባህሪያቸው በሚከተለው ሠንጠረዥ ላይ ቀርቧል፡፡