መስኖ


ለቲማቲም ልማት የመስኖ ውሃን ከወንዞች፣ ከምንጮች፣ ከጉድጓዶች፣ ከሐይቆችና ከልዩ ልዩ የማጠራቀሚያ ኩሬዎች ማግኘት ይቻላል፡፡ ችግኝ ከተዛመተ በኋላ ወዲያውኑ ውሃ መጠጣት ይኖርበታል፡፡ በቀላል አፈር ላይ ለመጀመሪያው ሦስት ሳምንታት በሳምንት ሁለት ጊዜ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ማሳውን በሳምንት አንድ ቀን ማጠጣት በቂ ነው፡፡ የውሃው መጠን ያለአግባብ ከበዛ የቲማቲም በሽታ  ሊከሰትና ምርቱም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ተክሉ እስኪጠወልግ ከተጠበቀ ደግሞ በምርቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡