መኸር እና ድህረ ምርት


  • መኸር(ምርት መሰብሰብ)
  • የጥቅል ጎመን ምርት ከማሳው የሚሰበሰበው በእጅ ነው፡፡ የጥቅል  ጎመን ራሶቹ ጥብቅ ሲሆኑ ይቆረጣሉ፡፡ የምርት መሰብሰቢያ ወቅትም  ለጎመኑ ጥራት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሆነም በጠዋት ክፍለጊዜ መሰብሰብ  ይመከራል፡፡ የተወሰኑ የጎመን ዝርያዎች ሲሰበሰቡ ተጨማሪ ልባስ ቅጠል እንዳላቸው ቢቆረጡ በመጓጓዝ ወቅት ጥሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን ታሽገው  ለገበያ ለሚቀርቡ ጎመኖች ከላይ ያሉት ትርፍ ቅጠል ልባሶች  ስለማያስፈልጉ ጎመን ራሱ ከፍ አድርጉ ከግንዱ ላይ መቁረጥ ይቻላል፡፡ ምርት ከተሰበሰበ በኋላ የጎመን ስር ግንዱን በአፈር ውስጥ መተው  የለብንም ምናልባት በማሳው ላይ በተባይና በነፍሳት አማካኝነት  ብክለትን ይፈጥራል፡፡ ዝርያዎቹ እኩል ካላደጉ በመስኖና በሰው ሀይል በእያንዳንዱ ምርት  መሰብሰቢያ ቀን ከመጀመሪያው ምርት መሰብሰቢያ ቀን በኋላ  ተጨማሪ ወጪን ያስከትላል፡፡
  • ድህረ ምርት(ምርት ከተሰበሰበ በኋላ)

ከተቻለ የጥቅል ጎመን ምርት ባልተጨናነቀ መልኩ ጥሩ አየር  በሚያስገባ ፕላስቲክ ማጠራቀሚያ ውስጥ መሰብሰብ፣ በጥብቅ ሁኔታ  ውስጥ ደግሞ ሳጥን መጠቀምና ጥላ ስር ወይም በመጋዘን ውስጥ  ማቆየት፣ የጥቅል ጎመን ከተሰበሰበ በኋላ ለፀሐይ ብርሃን ሳይጋለጥ  በጥላ ስር ማቆየት ያስፈልጋል፣ በእርሻ ቤቶች ጥላንና ቀዝቃዛ አየርን በማዘጋጀት የጎመኑን አዲስነት፣  ጥራት ጠብቆ በደረጃ በመመደብ እና በጊዜያዊ ማቆያ በማቆየት  ለገበያ ማቅረብ፡፡

  • የጥቅል ጎመን ምርት ከተሰበሰበ በኋላ አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች 

በ0 ዲሴ እና 98 በመቶ ተመጣጣኝ እርጥበት ባለበት ሁኔታ ማድረግ  እስከ 2 ሳምንታት በጥ ሁኔታ እንዲቆይ ያደርገዋል፡፡ (የጥቅል ጎመንን  በዝቅተኛ እርጥበት ማቆየት መጠውለግንና መበላሸትን ይፈጥራል፡፡) ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ለተጠቃሚው በሁለት ቀናት ውስጥ ቢደርስ  ይመከራል፡፡ ምርት ተሰብስቦ ከተከማቸ በኋላ ለተጠቃሚው ገበያ የሚደርስበት ጊዜ በጣም አጭር መሆን አለበት፡፡ ትክክለኛ የመጓጓዣ አይነት የጎመኑን የመቆያ ጊዜና ዋጋ እንደተጠበቀ  ያደርጋል፡፡ ውሃ እንዳያጣ መጠበቅ አለበት፡፡ ተሽከርካሪዎች በፀሀይ ላይ መቆም የለባቸውም፡፡ ምርቱም ሽፋን በማልበስ መጠበቅ አለብን፡፡  ከተቻለ ማቀዝቀዣ ክፍል ያላቸውን መጫኛ መኪናዎች መጠቀም፡፡  ማቀዥቀዣ ክፍሎችን ወይም ሌላ ማቆያ ዘዴዎቸን መጠቀም ካልተቻለ  ጎመኑ ከተሰበሰበ በኋላ ወዲያ መሸጥ ያስፈልጋል፡፡ የጥቅል ጎመን ለመበስበስ የተጋለጠ ስለሆነ የበሰበሱ አትክልቶች  አካባቢ ማቆየት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም አረንጓዴ ቀለሙን  ያሳጣዋል እና የመርገፍ(መበስበስ) ሁኔታን ይፈጥራል፡፡