መግቢያ


በማምረት የአገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል ይታመናል፡፡ ደብር ዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል የወይን ፍሬ በውስጡ የተለያዩ ቫይታሚኖች፣ ማዕድናት እና ካርቦሃይድሬት (ስከር) አለው፡፡ እነዚህን ንጥረ ነገሮች በተለይ ከዘቢብና ጭማቂ በቀጥታ ማግኘት ስለሚቻል ሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ እንደሆነ ይ፺መናል፡፡ በተጨማሪም የወይን ፍሬ ለወይን ጠጅ  መጥመቂያ፣ ለዘቢብ፣ ለገበታ እሸት፣ ለጭማቂና ከሌሎች ፍራፍሬዎች ጋር ተደባልቆ ለኮክቴል ያገለግላል፡፡ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኘው የወይን ምርት አብዛኛው ለወይን ጠጅ መጥመቂያ ይውላል፡፡ በዚህ መልክ የሚጠመቀው የወይን ጠጅ በዓይነትና በጥራት ከፍተኛ በመሆኑ ለውጭ ሀገር ገበያ ተፈጊነት አለው፡፡ ይሁን እ፺ንጂ የወይን ፍሬ ምርት አናሳ በመሆኑ የውጭ ገበያን ፍላጎት ለማሟላት አልተቻለም፡፡ ነገር ግን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት፣ ለኬክ መስሪያ፣ ለአገር ውሰጥ የወይን ጠጅ መጥመቂያ የሚውል እና የውጭ አገርን የወይን ጠጅ ፍላጎት ጥያቄ ለማስተናገድ እንዲሁም ከውጭ አገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በብዛት የምናስገባውን ዘቢብ አገር ውስጥ በጥራትና በብቃት  ለተለያዩ ጥቅም ሊውሉ የሚችሉ የተለያዩ የወይን ተክል ዝርያዎችን ከውጭ አገር በማስገባትና አገር ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ገብተው በተለያዩ አካባቢዎች በመመረት ላይ ያሉትን ዝርያዎች በማሰባሰብ ለአገራችን ተስማሚ የሆኑትን ለማወቅ ምርምር በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡