መግቢያ


ፓፓያ በኢትዮጵያ በወይና ደጋና ቆላ – ቀመስ አካባቢዎች በዝናብም ሆነ በመስኖ በመመረት ላይ ይገኛል፡፡ ፓፓያ የሞቃት አካባቢ ተክል በመሆኑ ውርጭ ባለባቸው አካባቢዎች አማካይ የሙቀት መጠኑ ከ12 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች ከሆነ ዕድገቱ ከመገታቱም በላይ የሚሰጠው ምርት አስተማማኝ አይሆንም፡፡ ሙቀቱ ከ13 እስከ 4ዐ ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ አካባቢ ፓፓያ በጥሩ ሁኔታ  ይመረታል፡፡ ባሁኑ ወቅት ፓፓያ በመጠኑ በጓሮ፣ በግልና በመንግስት እርሻዎች በስፋት እየተመረተ ለአር ውስጥ ገበያ አልፎ አልፎ ደግሞ ለውጭ ገበያ ይውላል፡፡ ለውጭና ለአገር ውስጥ ገበያ ተፈላጊ ዝርያ፤ ዘመናዊ የመስክ አያያዝ፤ የምርት ጥራትና የአያያዝ፤ የድህረ ምርት ፓኬጂንግ ሁኔታዎች ከተሻሻሉ የፓፓያ ምርት ለጎረቤት አገሮች ብሎም ለአውሮፓ ገበያ በማቅረብ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት ይችላል፡፡