ድንች በኢትዮጵያ ደጋና ወይና ደጋ አካባቢዎች ይመረታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1885 ዓ.ም በጀርመናዊ የእጽዋት ሊቅ ሺምፐር አማከኝነት ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የሚገመተው ይህ ሰብል በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶ ከ16ዐ ዐዐዐ ሄክታር በላይ በየዓመቱ በዝናብ እና በመስኖ ይለማል፡፡ የአማካይ ምርቱም በሄክታር 8ዐ ኩንታል ብቻ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ድንች ሰፋ ባለ የአፈር ዓይነት የሚበቅል ቢሆንም ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ግን በቀላሉ የሚጠፍ ፣ አሸዋማ ለም (የሆነ አፈር ይመረጣል፡፡ መረሬና ጥቁር በሆነ አፈር ላይ የድንች ምርት አነስተኛ ነው፡፡ የዝናብ መጠኑም በዓመት ከ75ዐ – 1ዐዐዐ ሚ.ሜ ሆኖ የተስተካከለ ስርጭት ይፈልጋል፡፡
ኢትዮጵያ ካላት ሰፊ ተስማሚ የአየር ንብረትና የአፈር ዓይነት አንፃር የድንች ምርት በስፋት ማምረት ይቻላል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ምርታማነቱ ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ሲነፃፀር ዝቅተኛ ነው፡፡ ለዚህ ዝቅተኛ ምርት ዋና ዋና መሰናክሎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን የምርት መሰናክሎች በማቃለል ምርታማነቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ለማፍለቅ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት የድንች ምርምርን በብሔራዊ ፕሮጀክት ደረጃ አደራጅቶና ለአፈጻጸሙ ስልት ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ልዩ ልዩ የምርምር ሥራዎችን በፌደራልና በክልል ምርምር ማዕከላት እንዲሁም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ከፍተኛ ግንኙነት በመፍጠር እየሰራ ይገኛል፡፡ እስካሁን በተደረጉ የምርምር ጥረቶች የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች በአጭሩ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡