ማዳበሪያ


የወይን ተክል ስሮች መሬት ውስጥ እስከ 5 ሜ. ጥልቀት ድረስ የማደግ ጸባይ እንዳላቸው ቢታወቅም ተክሉን በአብዛኛው የሚመግቡት ከ 2ዐ እስከ 6ዐ ሣ.ሜ ጥልቀት አካባቢ የሚገኙት ስሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ በየጊዜው ማዳበሪያ መስጠት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ምንም እንካ ፖታሽ  የተባለው ንጥረ ነገር ምርትን የማሳደግና የተክሎችን ተፈጥሮአዊ የበሽታ መከላከል ሃይል እንደሚጨምር በጥናት ቢረጋገጥም በአገራችን በተለይ በፖታሽ ማዳበሪያ የመጠቀም ልምድ የለም፡፡

          ሰንጠረዥ 1. ለወይን ተክል የማዳበሪያ ዓይነት እ፺ና መጠን

ንጥረ ነገ`ተክሉ የሚወስደው ፱ኪ.ግ በሄክታር)መተካት ያለበƒ
ናይትሮጂ”90-10140-200
ፎስፈረe30-45100-150
ጬታi120-150180-240
ማግኒዚምÁ50-6070-90

የወይን ተክል ማደግ እንደጀመረ ማዳበሪያ ይጨምራል፡፡ ናይትሮጂን የተባለውን ማዳበሪያ መጠኑን በመክፈል ሁለት ጊዜ መጨመር ያስፈልጋል፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ ከአራቱ ሶስቱ እጅ (75 በመቶ) ይደረጋል፡፡ ቀሪው ከአራቱ አንደኛው (25 በመቶ) ደግሞ ተክሉ በሚያብበት ወቅት በማድረግ አጥጋቢ ውጤት ማግኘት ይቻላል፡፡