ማዳበሪያ


አንዳንድ ማሳዎች በተፈጥሯቸው ለም በመሆናቸው ያለምንም ተጨማሪ ነገር ጥሩ ምርት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ሰብሉ የተጠቀመበትን ንጥረ ነገር ወደ አፈሩ መመለስ በቀጣይነት ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ነው፡፡ ለከፍተኛ ምርትና ጥራት ፓፓያ የናይትሮጂንን ንጥረ ነገር በከፍተኛ ደረጃ የፎስፎረስን ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ ይፈለጋል፡፡

ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎች ዋጋቸው ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ለተክሉ የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አያሟሉም፡፡ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች (ፍግ፣ ብስባሽ፣ አመድ፣ ወዘተ) ይገኛሉ፡፡ ውድ አይደሉም፣ ተፈጥሮን አይበክሉም፣ የአፈሩን የውሀ  መያዝ ችሎታን ከፍ ያደርጋሉ እና አፈሩ ለሥራ ተስማሚ እንዲሆን ይረዳሉ፡፡ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በአግባቡ ለመጠቀም በአካባቢ ከሚገኝ ባለሙያ ምክር ማግኘት ይጠቅማል፡፡ የሰው ሠራሽ ማዳበሪያ መጠቀም ግዴታ  ከሆነ በመጀመሪያ አፈሩ ምን እንደሚጐድለውና በተለያየ የተክሉ የዕድገት ደረጃ ምን እንደሚያስፈልገው ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለሁሉም ቦታ አንድ ዓይነት ማዳበሪያና አንድ ዓይነት መጠን ስለማይታዘዝ ከተቻለ የአፈርንና የቅጠል የንጥረ ነገር ይዘት በላቦራቶር ማረጋገጥ ጠቃሚ ነው፡፡