ምርት መሰብሰብና ማከማቸት


ለውዝ ለነቀላ መድረሱን እንደ ዝርያው ባህሪ በተለያየ መንገድ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች ሲደርሱ ቅጠላቸው ወደ ቢጫ መልክ ይቀየራል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ቅጠላቸው አረንጓዴነቱን እምብዛም ሳይቀይር ይደርሳሉ፡፡ ስለዚህ በትክክል መድረሱን ለማወቅ ቆፈር አድርጎ ከተክሉ መካከለኛው ግንድ ስር ካሉት የዘር ከረጢቶች አንድ ወይም ሁለት በመውሰድ መክፈትና የውስጠኛው የከረጢት ክፍል ወደ ቡናማ መልክ መቀየሩን በመለየት ለነቀላ መድረሱን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከደረሰ በኋላ በእጅ፣ በፎርካ፣ በመቆፈርያ ወይም ለለዉዝ በተዘጋጀ በትራክተር በሚጎተት ማሽን መንቀልና በፀሐይ በደንብ አድርቆ በጆንያ መሰብሰብ ያሻል፡፡ የተሰበሰበው ዘር እርጥበት በሌለበት ክፍል መከማቸት ይኖርበታል፡፡ ከአንድ ወር በላይ የሚቀመጥ ከሆነ ሳይፈለፈል ቢከማች ከተባይ ጥቃት ይድናል፡፡