ምርት መሰብሰብ እና ማከማቸት


ሀ) ምርት መሰብሰብ

የምርት መሰብሰቢያ ጊዜ ሲደርስ የታችኛው ቅጠሎች እና የቅጠሉ ጫፍ እየደረቀ ይመጣል፡፡ ከአጠቃላይ ቅሎች 2/3 በግማሽ ሲደርቅ ምርቱን መሰብሰብ ይቻላል፣ ኩርት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅ፣ ከ2-3ቀናቶችም በመስክ እንዲደርቅ ማድረግ አለብን፡፡

ለ) ማከማቸት

መታየት ያለበት በጣም አስፈላጊው ሁኔታ እርጥበት ነው፡፡ የነጭ ሽንኩርት ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት 80 በመቶ እርጥበት አለው፡፡ ስለሆነም

  ለረጅም ጊዜ ለማቆየት እርጥበቱን እስከ 65 በመቶ ድረስ በማድረቅ ማቆየት ይቻላል፣ ለተፈጥሮአዊ ማድረቅ ሂደት ምርቱን ከሰበሰብን በኋላ አየር በደንብ  በሚናፈስበት ጥላ ስር የነጭ ሽንኩርቱን ማንጠልጠል፣ በአንድ ላይ ማሰር  ወይም በወንፊት ጨርቅ ውስጥ በማድረግ በአንድ ላይ ማንጠልጠል፣ረጅም ጊዜ የማቆየት ሁኔታ፡- ከ0-3ዲሴ፣ አርኤች 65-70 በመቶ ከተፈጥሮአዊ የማድረቅ ሂደት በኋላ