ምርት አሰባሰብ


አጨዳና ዉቂያ

ቅጠሉ ሲደረቅና አብዛኛዎቹ ጓዮች (capsule ) ወደ ቡናማ መልክ ሲቀየሩ እንዲሁም ዘሩ በጓዮቹ ውስጥ የመንኮሻኮሽ ድምዕ ሲያሰማ የምርት መሰብሰቢያዉ ጊዜ መድረሱን ያመለክታል፡፡ በዚህ ጊዜ የዘር እርጥበት በ10 እና 15 በመቶ መካከል ይደርሳል፡፡ ከተዘራበት ጀምሮ እስኪደርስ በአማካይ ከ90-150 ቀናት ይወስድበታል፡፡ ይህ የመደረሻ ጊዜ እንደየአካባቢው ሁኔታ ይለያያል፡፡ የአገራችን ገበሬዎች አብዛኛውን ጊዜ ተክሉን በመንቀል ወይም በማጨድ እስከ ሦስት ሳምንታት ድረስ እንዲደርቅ በማሳው ላይ ያቆዩታል፡፡ በደንብ ከደረቀ በኋላ ለውቂያ በተዘጋጀ ንፁህ አውድማ (ሸራ) ላይ በማድረግ በከብት ወይም በእንጨት እየደበደቡ ይወቁታል፡፡ ሰፋፊ ለሆኑ እርሻዎች ስንዴንና ገብስን አደው በሚወቁ ተሽከርካሪዎች (combine harvester ) በመጠቀም መሰብሰብ ይቻላል፡፡

ክምችት

አብዛኛውን ጊዜ ተልባ የክምችት ችግር የለበትም፡፡ በክምችት ወቅት በተባይ አይጠቃም፡፡  የዘር እርጥበቱ ከ9 በመቶ በታች ሆኖ፤ አየር እንደልብ በሚዘዋወርበት ቀዝቃዛ ማከማቻ (ጎተራ፣ ጆንያ፣ ወዘተ) ውስጥ ለረጅም ጊዜ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

የጥራት ሁኔታዎች

የተልባ ዘርን የጥራት ደረጃዎች የሚወስኑት የታለመለት ዓላማ ወይም አገልግሎት ነው፡፡ ለምሳሌ በቀጥታ ለምግብነት፣ ለምግብ ዘይት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ወዘተ በሚውሉበት ጊዜ የተለያዩ የቅባት፣ የፕሮቲን፣ የአዮዲንና የፋቲ አሲድ ይዘቶች እንዲዴሟሉ ይጠበቃል፡፡ ዘሩ በቀጥታ ለምግብነትና ለኢንዱስትሪ የሚውል ከሆነ ከ36-42 በመቶ ቅባት፣ ከ18-24 በመቶ ፕሮቲን፣ ከ177-196 የአዮዲን መጠንና ከ40-60 በመቶ  ሊኖሌኒክ ጥሩ የጥራት ደረጃን ያመለክታሉ፡፡ ለምግብ ዘይት የሚውሉት ዝርያዎች ግን የሊኖሌኒክ ይዘታቸዉ ከ5 በመቶ በታች መሆን ይኖርበታል፡፡ በአጠቃላይ ከማናቸውም ቆሻሻዎች (አፈር፣ አረም፣ ወዘተ) የፀዳና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ዘር በገበያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ አለው፡፡

ተሻሽለው የተለቀቁ የተልባ ዝርያዎችና ባህሪያቸው

ዝርÃየመድረሻ ቀናTምርት (ኩ/ሄ)የቅባት መጠን (%)
በምርምር ማúበገበሬ ማú
 ሲአይ-152514614.308.1038.5
 ሲአይ-165214613.608.8038.6
ጭላሎ14016.709.0035.2
በላይ-9614116.809.0036.3
በረኔ14016.179.1037.0
ቶሌ14316.9010.0036.0