ሰብል ጥበቃ


አረም

ለውዝ በተዘራ ከ3ዐ እስከ 35 ቀናት ውስጥ ካልታረመ ጥሩ ምርት አይሰጥም፡፡ በዚህ ወቅት አንዴ ማረምና ለማበብ ሲቃረብ ደግሞ መኮትኮትና አፈር መታቀፍ ይኖርበታል፡፡ አፈር ማሰታቀፉ ፍሬ የሚይዙ ቅርንጫፎች በቀላሉ አፈር እንዲያገኙ ይረዳል፡፡ በምናሳቅፍበት ጊዜ የተክሉን መሀል ሳንሸፍን በጥቂቱ ከጎን ጎኑ መሆን አለበት፡፡ በዘር መሰብሰቢያው ወቅት ማሳው ከአረም የፀዳ መሆን አለበት፡፡ ፀረ-አረም መድሀኒት መጠቀም ሲያስፈልግ ፓቶራን 3 ኪ.ግ. በሄክታር ወይም ዱያል 2 ኪ.ግ. በሄክታር መርጨት ይቻላል፡፡

በሽታ

በአገራችን ከተመዘገቡት የለውዝ በሽታዎች ውስጥ ዋግ አና የቅጠላ ቅጠል ጠቃጠቆ  ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ፍቱን መፍትሄያቸውም በሽታዎችን የሚቋቋም ዝርያ መጠቀም ነው፡፡ ሌላው ለውዝ ከመድረሱ በፊትና ደርሶ ከተሰበሰበ በኋላ ወይም እርጥበት በበዛበት ማከማቻ ውስጥ የሚፈጠር ሻጋታ አፍላቶክሲን የተባለውን መርዛማ  ኬሚካል የሚያስከትል በሽታ ነው፡፡ ይህንን ለመቆጣጠር ሰብሉ እንደደረሰ መሰብሰብና ዝናብ ሳይነካው አድርቆ እርጥበት በሌለበት ቦታ ማከማቸት ያስፈልጋል፡፡

ተባይ

ለውዝን ከሚያጠቁ ተባዮች ውስጥ ክሽክሽ፣ ቦልወርም፣ ጃሲድ፣ ትሪፕስና ምስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ማሳን በማፅዳት፣ በወቅቱ በመዝራትና እንደ ማርሻል እና ኢትዮሰልፋን የመሳሰሉ ፀረ-ተባይ መድቨኒቶችን በመጠቀም ልንቆጣጠራቸው እንችላለን፡፡

ሠንጠረዥ 1. የለውዝ ምርጥ ዝርያዎች

ዝርÁበመስ•አነስተኛ ዝናብ ባላቸውበቂ ዝናብ ባላቸውየዘይት መጠን (በመቶኛ)ለመድረስ የሚፈጀው ቀናƒተስማሚ ቦቆዎ‹
ሹላሚ´5817294414®ለአብዛኛው የአገሪቱ ቦቆዎ‹
ኤን ሲ ፎር ኤክስ314614®በተለይም ዝናብ አጠር ለሆኑ ቦታዎች (ባቢሌ፣ ጉርሱም)
ኤን ሲ ስሪፎርቲስ]53254814®በተለይም ዝናብ አጠር ለሆኑ ቦታዎች (ባቢሌ፣ ቆቦ፣ ጉርሱም)
ሮv68334915®በመስኖ ወይም በቂ እቺርጥበት ላላቸው (ወረር፣ ምስራቅ ወለጋ)
ሰዲ3212521ዐ®አጭር የዝናብ ወራት ላላቸው (ሚዔሶ)
ማኒፒንተ`4835155በቂ ዝናብ ላላቸው ፺በለስ፣ ፓዌ)
ሎጤ59245213®መካከለኛ ዝናብ ላላቸው (ጎፋ)
ቡልm65122253135መካከለኛ ዝናብ ላላቸው (ጎፋ)
ወረር 9615523184611®አጭር የዝናብ ወሪት ላላቸው (ሚዔሶ)
ወረር 96257262148128መካከለኛ ዝናብ ላላቸው (ጎፋ፣ ባቢሌ)
ወረር 9632246128ድርቅ ለሚያጠቃቸው (ሚዔሶ፣ ቆቦ)
ወረር 9642146128ድርቅ ለሚያጠቃቸው (ሚዔሶ፣ ቆቦ)