ሰብል ጥበቃ


በሽታ

ዋና ዋና የጉሎ በሽታዎች አጠውልግ፣ ምችና ዋግ ሲሆኑ በጣም  አውዳሚው አጠውልግ ነው፡፡ ይህን በሽታ መከላከል የሚቻለው በማሳ ፈረቃ ሲሆን ደጋግሞ መዝራት ግን ለበሽታው ያጋልጣል፡፡ በሽታው በከፍተኛ ዝናብና የአየር ርጥበት ይባባሳል፡፡ የጉሎ ዝርያዎች ይህንን በሽታ የመቋቋም ተፈጥሮአቸው ይለያያል፤ በመረጣ በሽታውን የሚቋቋሙትን መለየትና ማውጣት ዋናው መከላከያ ዘዴ ነው፡፡