ሰብል ጥበቃ


የበሽታ  ቁጥጥር

ዋና ዋናዎቹን የድንች በሽታዎች ዋግ ቫይረስ እና ግንድ አጠውልግ ናቸው፡፡ የእነዚህን በሽታዎች ጥቃት ለመቀነስ፣

  • በሽታን የሚቋቋሙ ዝርያዎች መጠቀም
  • መድሃኒት መርጨት፤ ለዋግ ኤም ሪድሚል ኤም 2 ኪ.ግ በሄክቆር የበሽታው ምልክት እንደቆየ መርጨት
  • ንፁህ የድንች ዘር መጠቀም
  • የሰብል ፈረቃን መጠቀም
  • ድንች በተተከለበት አካባቢ ተመሣሣይ በሽታ  የሚያጠቃቸውን ተክሎች መንቀልና የድንች መጋዘንን በንፅህና መያዝ ናቸው፡፡

የተባይ ቁጥጥር

በድንች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ተባዮች የድንች ቢራቢሮ ግንድ ቀንጥስ፤ ክሽክሽ ናቸው፡፡ የመከላከያ መንገዶቹም፣

  • መጋዘንን በንፅህና መያዝ
  • ማሣን ከአስጠጊ አረሞች ማፅዳት
  • ከቫይረስ በሽታ  ለመከላከል ክሽክሽ በማይበዛበት ጊዜ ዘር ማባዛት
  • ፀረ ተባይ መድሃኒቶችን መጠቀም