ሰብል ጥበቃ


በሽታ

በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ትልቁ የፓፓያ ችግር በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ አንትራክኖስ የተባለው በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ፍሬውን በማጥቃት ተቀባይነቱን ያሳጣዋል፡፡ ሲጠነክርም ደግሞ ቅጠሉን በማጥቃት ተክሉን ይገድላል፡፡ በሽታውን ለመቀነስ አስፈላጊውን ማዳበሪያ መጨመር የመስኖ ውሃ  ማጠጣትና ፅዳት ማድረግ እና ዘርን ጤናማ ከሆነ ተክልና ፍሬ ብቻ መውሰድ ይረዳል፡፡ በበሽታው የተጠቃውን የተክል ክፍል ስብስቦ ማቃጠል ወይም መቅበር በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል፡፡

ፓውደሪ ሚልዲው የተባለው በሽታ ደግሞ ሞቃ፺ምና እ፺ርጥበት ባላቸው ቦ፺ዎች ችግር ይፈጥራል፡፡ በበሽ፺  የተበከሉ የተክሉ ክፍሎችን ማስወገድና ካራቴ የተባለውን  ሚካል 225 ግራም ከ8ዐዐ ሊትር ው፺  ውስጥ በጥብጦ መርጨት በሽ፺ውን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ ው፺  በሚጠጣበት ወቅት የመስኖው ው፺  ከአንድ ተክል ወደሌላው በመሄድ በሽ፺ውን እ፺ንዳያዛምት በየዛፉ ሥር ው፺ውን መከተር ያስፈልጋል፡፡ በርካ፺  የአፈር ውስጥ ው፺ና ከ2ዐ እ፺ስከ 3ዐ ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሙቀት ባላቸው ቦ፺ዎች ደግሞ ተክሉ የፓፓያ ፍይቶፍትራ ለሚባል በሽ፺  ያጋልጣል፡፡ ው፺ውን ማጥፈፍ የሰብል ፈረቃና ትክክለኛ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴን መጠቀም ችግሩን ይቀንሳል፡፡ ችግሩ ከበዛ ቦርዶክስ ሚክስቸር የተባለው  ሚካል መጠቀም ይረዳል፡፡

በቅርብ ጊዜ ደግሞ ከመሬት 1ዐ እ፺ና 2ዐ ሣ.ሜ. አካባቢ የግንዱን ዙሪያ እያቆሰለና እየከረከረ ግንዱን አቅጥኖ የሚሰብር ጉሞሲስ የተባለ አዲስ በሽ፺   ፺ይቷል፡፡ ይህን በሽ፺  ለመከላከል ሪዶሚል የተባለውን  ሚካል መጠቀም ይቻላላ፡፡ በማንኛውም ጊዜና ቦ፺ የፓፓያ ተባይ ሲከሰት ችግሩን በአፋጣኝ በአቅራቢያ ለሚገኙት የዕፅዋትና በሽ፺ ጥበቃ ባለሙያዎች ማሳወቅና መፍትሄ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

አረም

በተክሎቹ ሥር ያለውን አረም በ፺ጅ በመንቀልና በጥንቃቄ በመሣሪያ ማስወገድ ከሰብሉ ጋር ያለውን ውድድር ከመቀነሱም በላይ ለተባይና በሽ፺  መቆያ እ፺ንዳይሆን ይረዳል፡፡ በተጨማሪም በተክሉ ሥር ከአካባቢው የሚገኝ የተክል ቅሪት ጉዝጓዝ ማድረግ አረም እ፺ንዳይበቅል ከመከላከሉም በላይ ው፺  ከአፈሩ ላይ እ፺ንዳይተን፣ የአፈሩ ሙቀት እ፺ንዳይዋዥቅና በሚበሰብስበት ጊዜ የአፈሩን ለምነት እ፺ንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ፀረ-አረም መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ዓይነቱን፣ መጠኑንና አጠቃቀሙን ከአቅራቢያ ከሚገኙ ባለሙያዎች መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ንፋስና በረዶ

ፓፓያ በተፈጥሮው ደካማ ግንድ፣ ሰፋፊ ቅጠልና ከባድ የፍሬ ጫና ስላለው ለንፋስ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ከተቻለ ነፋስ በማይበዛበት አካባቢ ማምረት ያለበለዚያም ግን ንፋሱ በሚመጣበት አቅጣጫ የንፋስ መከላከያ ማዘጋጀት ወሳኝ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔ፺ በረዶና ከፍተኛ ዝናብ የሚበዛበትን አካባቢ ለፓፓያ ማምረቻነት መጠቀም አይመከርም፡፡

ደባል ሰብል

ፓፓያ ፺ንደተተከለ ማሳውን ሁሉ ስለማይሸፍን በመስመሮች መካከል ዓመ፺ዊ ሰብሎችን ማምረት ይቻላላ፡፡ ለዚህ ተግባር የሚመረጡ ሰብሎች በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሥራቸው ጥልቀት የሌለውና ሲመረቱ የፓፓያውን ስሮች የማይጎዱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የፓፓያ ተክል በማሳ ላይ ከ2 እ፺ስከ 3 ዓመ፺ት ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በብርቱካን፣ ማንጎ፣ አቮካዶና የመሳሰሉት ማሳ ላይ በመጀመሪያዎቹ ዓመ፺ት ሊመረትና ተጨማሪ ጥቅም ሊሰጥ ይችላል፡፡