ሰብል ጥበቃ


አረም


ቦቆሎ ከብቅለት እስከ ዛላ ማወጣት ድረስ በአረም ከተበላ ከፍተኛ የምርት መቀነስ ያስከትላል፡፡ ስለዚህ በቆሎ ከተዘራ የመጀመሪያውን በ25-3ዐ ቀናት እና ሁለተኛውን ከ55-6ዐ ቀናት ውስጥ መቆረም ይኖርበቆል፡፡ በተጨማሪም ዘግይተው የሚበቅሉ አረሞችን ለመከለከል መመንጠር አስፈላጊ ነው፡፡ የግብርና ባለሙያ በማማከር እንደ ፕሪማግራም 83 በመቶ እና ጌሣፕሪም 71 በመቶ ከ4-5 ሊትር በሄክታር ከብቅለት በፊት በመርጨት አረምን መከላከል ይቻላል፡፡


ተባይ


ስብሉ በተለያዩ የመስክና የጎተራ ተባዮች ይጠቃል፡፡ አገዳ ቆርቁር፣ ምስጥ፣ ተምች እና ክሽክሽ በቆሎን በመስክ ላይ
ከሚያጠቁት ተባዮች ዋነኞቹ ሲሆኑ በጎተራ ደግሞ ነቀዝና የቺሳት እራት ይገኙበቆል፡፡


አገዳ ቆርቁር


የአገዳ ቆርቁር እየቺሳት እራት ክብና ነጭ እንቁላሎችን አዲስ በተዘሩ ቡቃያዎች ላይ ትጥላለች፡፡ እንቁላሎቹ ለመፈልፈል አስር ቀን ይፈጅባቸዋል፡፡ የተፈለፈሉት እጮች ግራጫማ መልክ ሲኖራቸው እያደር ጠቆር ያለግራጫ ወይም ጥቁር መልክ ይኖራቸዋል፡፡ ጉዳት የሚያደርሱት እጮች ሲሆኑ እንደተፈለፈሉ ቅጠሉን በመብላት ቀዳዳ ይተዋሉ፡፡ ከዚያም ወደ ሙሽራው ዘልቀው በመግባት ሙሽራው እንዲሞት ያደርጉቆል፡፡ በመቀጠልም ግንዱን ቦርቡረው ወደስሩ አካባቢ ይቀመጡና ለቺሳት እራት መውጫ የሚሆን ቀዳዳ ይተዋሉ፡፡ እጮቹ በአመቺ የዝናብ ወራት ከተደበቁበት የበቆሎ ወይም የሣር አገዳ ውስጥ ወደኩብኩባነት ይቀየራሉ፡፡ እንደአየሩ ፀባይ በ1ዐ ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ወደ እሳት እራትነት ይቀየራሉ፡፡

አገዳ ቆርቁርን ለመከላከል የሚከተሉትን ባህላዊ ዘዴዎች መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

 • ምርት ከተሰበሰበ በኋላ የሚቀረውን የሰብሉን አገዳ ጨፍጭፎ ከአፈር ጋር አደባልቆ ማረስ ወይም ከማሳ አንስቶ
 • ከሦስት እስከ አራት ሳምንቆት ፀሃይ ላይ በማስጣት አገዳ ውስጥ ያለውን ኩብኩባና እጩን መግደል
 • ማሳዎችን በሚገባ ማረስና ንፅህናቸውን መፎበቅ፤ በአካባቢው የሚበቅሉ ወፈር ያለ ግንድ ያላቸውን የሣር ዝርያዎች ማስወገድ
 • የአገዳ ሰብሎችን በሌሎች ሰብሎች ማፈራረቅ
 • የአካባቢው አየር ፀባይ ለተባዩ ርቢ አመቺ ከሆነ የዘር ወቅትን ማስተካከል
 • ሌሎች ሰብለችን ከበቆሎ ጋር በማሰባጠር መዝራትና የመኖ ሳሮችን ፺ዴዝሞዲዬም እና ናፒየር፻ በማሳ ዙርያ መትከል ይህን ሁሉ አልፎ ተባዩ ከተከሰተ ፀረ-ተባይ መጠቀም አለብን፡፡ ነገር ግን ፀረ-ተባይ ከመጠቀማችን በፊት የተጠናከረአሰሳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
 • ቅጠሉ ላይ ርጭት የሚደረገውእጩ ወደ ሙሽራው ከመግባቱ በፊት መሆን ይኖርበቆል፡፡

ከፀረ-ተባይ መድሃኒቶች ውስጥ

 • ሳይፐርሜትሪን 1 በመቶ ሽርክት እየቆነጠሩ በሙሽራው መጨመር ፺ሰብሉ ከጉልበት በላይ መሆን ይኖርበቆል፡፡፻
 • ካርባሪል 85 በመቶ ዱቄት በውሃ በጥብጦ መርጨት
 • ኢትዮሱልፋን 5 በመቶ ዱቄት 5-8 ኪ.ግ. በሄክታር
 • ኢትዮሱልፋን 35 በመቶ 2-2.5 ሊትር በሄክታር35 በመቶ 2-2.5 ሊትር በሄክታር
 • ዲያዚኖን 1ዐ በመቶ ሽርክት እየቆነጠሩ በሙሽራው መጨመር


የቦቆሎ ነቀዝ


ነቀዝ የበቆሎን ፍሬ በመቦርቦር ዕንቁላሉን ሰብሉ በማሳ ላይ እንዳለ ወይም በክምችት ወቅት መጣል ይጀምራል፡፡የተጣሉ ዕንቁላሎች ከ3-5 ቀናት ወደ እጭነት ይለወጣሉ፡፡ እጩ እህሉን እየተመገበ ይቆይና በ25 ቀናት ወደኩብካባነት ይቀየራል፡፡ ኩብኩባው ፍሬውን ቦርቡሮ በመውጣት በጎተራ ውስጥ ወይም ከፍተኛ የመብረር ችሎቆ ስላለው ከጎተራ ውጭ ሰብሉን በማሳ ላይ እንዳለ ማጥቃት ይጀምራል፡፡ የበቆሎ ነቀዝ በቆሎን የሚያጠቃው በቺጭነት ወቅትና ከተፈለፈለ በኋላ ነው፡፡ የበቆሎ ነቀዝ ክብ ያልሆነና ያልተስተካከለ ቀዳዳ ሲተው የቺሳት እራት ደግሞ ወጥና ክብ ቀዳዳ ይተዋል፡፡ የበቆሎ ነቀዝ በሰብል ላይ የማያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስና የተፈለገውን ያህል ለማከማቸት የተለያዩ የመከላከያ መንገዶችን በስራ ላይ ዋልይቻላል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች አምራቾች በአካባቢያቸው በተለምዶና በቀላሉ የሚጠቀሙባቸው ናቸው፡፡

 • በተቻለ መጠን የዘር ልባሳቸውን ( ) የማይከፍቱ ዝርያዎችን መዝራት
 • ምርት ከመሰብሰቡ በፊት ሰብሉ የሚፈለገው የብስለት ደረጃ ላይ መድረሱን ማረጋገጥ
 • የተፈለፈለ እህል ወደጎተራ ከመግባቱ በፊት ፀሀይ ላይ በማስጣትና በሚፈለገው መጠን መድረቁን ማረጋገጥ፡፡
 • እህል የሚከማችባቸው ጎተራዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን አዲስ የተመረተ እህል ከመጨመሩ በፊት በደንብ ማፅዳት
 • ካለፈው የምርት ዘመን ቀሪ የምርት ክምችት ካለ አዲስ ከሚጨመረው ጋር አለማደባለቅ
 • ደርቆ ለክምችት የተዘጋጀ እህል ሸራ ላይ በማስጣት በበቆሎ፣ በአኩሪ አተር ወይም በኑግ ዘይት በአንድ ኩንቆል ዐ.5 ሊትር በመጠቀም ማሸት
 • ኒም ፺የድሬዳዋ ዛፍ፻ እና ፓይረትረምን ከበቆሎ ጋር ደባልቆ በማስቀመጥ የበቆሎ ነቀዝ የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ

በሽቆ


በቆሎ በተለያዩ የቅጠል፣ ግንድና ጭንቅላት በሽቆዎች ይጠቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ፈቆኝ የሆኑት የተለያዩ ጉዳት የሚያስከትሉት የቅጠል በሽቆዎች ናቸው፡፡ እነዚህን በሽቆዎች ለመከላከል በዋነኝነት በሽቆውን በከፍተኛ ደረጃ መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን መዝራት አስፈላጊ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ቢ.ኤች.-66ዐ፣ ቢ.ኤች.-67ዐ እና ኩለኒ የተባሉት ዝርያዎች ይገኙበቆል፡፡ ፀረ-ተባይ መድሃኒቶች ቤኖሚል ዐ.5 ኪ.ግ በሄክታር ቅጠል አድርቅን ( )፣ ማንኮዜብ 2 ኪ.ግ ንጥረ ነገር በሄክ በሄክታር ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ በአሥር ቀን ልዩነት መርጨት ተርሲከም ሊፍ ብላይትን ፺ ፻ እንዲሁም የማንኮዜብና ፕሮፖኮናዞል ድብልቅ 2 ኪ.ግ ንጥረ ነገር በሄክታር ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ በአስር ቀን ልዩነት መርጨት ኮመን ሊፍ ረስትን ( ) ለመከላከል ይረዳል፡፡

ፈረቃ

ሰብሉን ከሌሎች በተለይ ከኑግ፣ አኩሪ አተር፣ ስ ር ድንችና ከመሳሰሉት ሰብሎች ጋር አፈራርቆ በመዝራት የአፈር ለምነትን ከመጠበቅ ባሻገር የበቆሎን ምርት ሳይቀንሱ ተጨማሪ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡ ለፈረቃ የምንጠቀምባቸው ሰብሎች እንደምንጠቀመው የበቆሎ ዝርያና አካባቢው ይለያያሉ፡፡