በሽታንና ተባይን መቆጣጠር


በሽታንና ተባይን መቆጣጠር
የጥቅል ጎመን ነፍሳቶችና ተባዮች crickets, cutworms, flea beetles, saltmarsh caterpillars, aphids,  thrips, and cabbage looper. አንዴ ነፍሳት የጎመን ራስን ቀዶ ከገባ በኬሚካል ለመቆጣጠር አይቻልም ፡፡ ለሲስት ኔማቶድ ስለሚያጋልጥ ሹገር ቤትስን(ቁጫጭ) ተከትሎ  የጥቅል ጎመን መተከል የለበትም፡፡(Heterodera schachtii). ሻጋታዎች(Peronospora parasitica) እንዳይከሰቱ እርጥበትና ቀዝቃዛ  ሁኔታዎችን እንዳይቀጥሉ መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ ስር አበስባሽ(Xanthomonas campestris pv. campestris) አልፎ አልፎ በኢምፔሪያል ግዛቶች ይከሰታል፡፡ ከበሽታ ነፃ የሆኑ ዘሮችን መትከል ወይም ከበሽታ የፀዱ ንቅለተከላዎችን ማከናወን፡፡ (እባጭ) የጥቅል ጎመን ተፈጥሮአዊ መዛባት ሲሆን በቅጠሎች የውስጠኛ  ክፍል ቀዳዳዎችን በመፍጠር የሚከሰት ነው፡፡ የሚከሰተውም ከልክ  በላይ ውሃ በማጠጣት በይበልጥ በደመናማና እርጥበታማ በሆነ አየር  ጊዜ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በውጭኛው የቅጠል ክፍል  በመቀደድ ውጤት ይከሰታል፡፡የተጎዱ ተክሎች በሜካኒካል ጉዳት ወይም  በስነ ባህሪይ እንከን ይከሰታሉ፡፡ ወፎችና ነፍሳት ተክሉን በሚመገቡ ጊዜ  ለክስተቱ ምክንያት ይሆናሉ፡፡  

በሽታዎች

ምልክቶች
ከጤናማ ተክል ሲነፃፀር ዝቅተኛ አስተዳደግ በሽታው በተክሉ ላይ  የተስፋፋ መሆን፣ ጤናማ ያልሆነ  የስር ቅርጽ መኖር፣በርካታ እርጥበቶች መከሰት የሚከሰትበት ሁኔታዎች ከ80 በመቶ በላይ የሆነ የአፈር እርጥበት፣ ከ20-25ዲሴ የአየር ሙቀት፣ የአፈር አሲዳማነት ከ6.0 በታች ከሆነ ለክስተቱ ምቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ መከላከያ ዘዴ
አፈርን ከከፍተኛ እርጥበት መከላከል ካልሺየም ካርቦኔትን በመጠቀም የአፈር ፒኤች ከ7.2 በላይ እንዲሆን  መጠበቅ የተበከሉ ተክሎችንና አቸንፍር ነፍሳት መግታት ባዮሎጂካሊ መቆጣጠር ዘሩን በPseudomonas fluorescens ማከም፡፡ በኪግ ዘር 10ግ Pseudomonas fluorescens መጠቀም፡፡ በመቀጠልም ቡቃያውን 5ግ በሊትር መንከርና እና አፈሩ ላይ .5ኪግ/በሄክታር መጠቀምና  ከመትከላችን በፊት 50ኪግ ማዳባሪያ ጎን ለጎን መጠቀም፡፡
በኬሚካል መቆጣጠር
2ግ የሆነ ዘርን በሊትር Carbendazim ውህድ ውስጥ ለ20 ደቂቃዎች  መዘፍዘፍ፣ በዋናው መስክል ላይ ችግኞችን ዙሪያ አፈሩን በ Carbendazim 1ግራም በሊትር ውሃ ማራስ፣ ሰብል በሚቀያየርበት ጊዜ ክትትል ማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለ3 አመታት ማስወገድ፡፡  Pseudomonas fluorescens መጠቀም፡፡ በመቀጠልም ቡቃያውን 5ግ በሊትር መንከርና እና አፈሩ ላይ .5ኪግ/በሄክታር መጠቀምና  ከመትከላችን በፊት 50ኪግ ማዳባሪያ ጎን ለጎን መጠቀም፡፡

ፓይቲየም ብስባሽ

ምልክቶች

በቡቃያ ወቅት ጠባብ ግንድ መታየት፣ ቡቃያው ከደረሰ በኋላ  መሀል ቅጠል መበስበስ እና  በመጀመሪያ በላይኛው የአፈር  ክፍል ላይ መበስበስና ቡኒ ቀለም መሆን፤ ምልክቶቹ  የሚታዩት ለአፈር ቅርብ በሆኑ  ቅጠሎች ላይ ነው፡፡ የተበከለው  ቦታ ለስላሳ አይሆንም ሽታም አይኖረውም፡፡

መከላከያ ዘዴ

ጤናማ አፈር ላይ ቡቃያውን መትከል፣ ጥሩ የውሃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ ይህም ለረጅም ጊዜ የሚታመቅ  እርጥበትን ይከላከላል ፣ ከፍተኛ የሆነ ሙቀትንና በጣም ዝቅተኛ የሆነ አየርን ማስወገድ  በከፍተኛ ሁኔታ አጠጋግቶ አለመትከል፡፡

የሚከሰትበት ሁኔታዎች

የአየር ጠባዩ ሙቀት ከ20 ዲሴ በታች፣ ከፍተኛ የአፈር እርጥበት ሁኔታ  ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከ10ዲሴ በታች በሽታ አምጪ ተህዋስያን  በማይታዩበት ሁኔታ ይቆያሉ፣ ከ10ዲሴ በላይ ሲሆን ደግሞ ህይወት  ዘርተው ይታያሉ፡፡ በሽታ አምጪ ተህወስያኑ በውሃ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡  ጎመን ላይ ከደረሱ ከ2-3 ቀናቶች ውስጥ ጠቅላላ ጎመኑን ይወሩታል፡፡  በመስኖ አማካኝነትም ብክለቱ ሊፈጠር ይችላል፡፡

ጥቁር ነጠብጣብ

ምልክቶች

ዋና ምልክቶች ጥቁር ነጠብጣቦች በቅጠሉ ላይ ይታያሉ እና በነጠብጣ  ቦቹ አካባቢ ቅጠሉ ቢጫ ይሆናል፡፡ ምልክቶቹ አስከፊ እየሆኑ ሲመጡ  ቅጠሎቹ ይሞታሉ፡፡

የሚከሰቱበት ሁኔታዎች በሽታ አምጪ ተህዋስያኑ hyphae, ለመቆየት ይጠቀማሉ፡፡ ከዛ.

ምልክቶቹ በግንዱ፣ በቅጠሎቹና በዝንቡጦቹ ላይ ይከሰታል፡፡ መጀመሪያ ወቅት  በተክሉ ላይ ነጭ ዱቄት ይመስላል፡፡ ምልክቶቹ አስከፊ ሆኖ የሚመጣው  ቅጠሎቹ በሙሉ በዱቄት ሻጋታ ሲሸፈን ነው፡፡ በጣም አስከፊው ቅጠሎቹ ቢጫ ቡናማ ይሆኑና ኋላም ይሞታሉ፡፡ ምልክቶቹ ዝንቡጥ  ላይ ከሆነ ደግሞ ዘር ማፍራት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ የሚከሰትበት ሁኔታ በፕላስቲክ ቤት ውስጥ ዘር ማምረት ስራ ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ያመጣል  በሽታ አምጪ ተህዋስያኑ በዝናባማ ወቅት በፈንገስ መልክ ይከሰታሉ፣  ይህ የመጀመሪያ መጠቃትን ያመላክታል፡፡ ደረቅ በሆነ ፕላስቲክ ቤት ውስጥ በሽታው በአስጊ ደረጃ ሰታል  በተለመደ የእርሻ መስክ ላይ ክስተቱ እምብዛም ነው፡፡ መከላከያ ዘዴ የሞቱ ቅጠሎች፣ ግንዶችና ተክሎችን ማስወገድ፣  ከበቂ በላይ የናይትሮጂን ማዳበሪያ አለመጠቀም፣  የበዛ የድርቀት ኔታዎችን ማስወገድ፡፡  

መጠውለግ ምልክቶች

ከታች ተክሉ ቢጫ መሆን፣ ደካማ እድገትና መጠውለግ፣  በሽታው ከተስፋፋ ጠቅላላ ተክሉ ቢጫ ይሆናል እና ይጠወልጋል፣  የተክሉ ስር ቡኒ ይሆናል እና ይበሰብሳል፡፡

የሚከሰትበት ሁኔታ

ተህዋስያኑ በተበከሉ የተክሉ ህብረህዋስ ላይ ይኖራሉ ወይም በአፈር  ላይ በእንቁላል መልክ ወይም በዘር መልክ ይቆያሉ፣ ተህዋስያኑ በውሃ ብቻ ሳይሆን በማረሻ ወይም በሰው እግር ይዛመታሉ፣ በተህዋስያኑ የተጠቃ ተክል ይበሰብሳል ወይም ጠባሳ(መጠውለግ)  ያሳያል፣ ለብክለቱ አመቺ የሚሆነው የአየር ጠባይ ከ24ዲሴ በላይ ሲሆን ነው  ከ16 ዲሴ በታች ወይም ከ33ዲሴ በላይ ሲሆን በሽታ አይከሰትም፡፡

መከላከያ ዘዴ የአፈሩን አሲዳማነት pH 6.5~7.0 መልኩ መቆጣጠር፣  በበሽታ በተጠቃ መሬት/እርሻ መስክ/ ላይ አለመትከል፣  የተክሉ ስር እንዳይጎዳ መጠበቅ፡፡

ጥቁር ብስባሽ ምልክቶች

በመጀመሪያ ጊዜ ቅጠሉ ቢጫ ጠባሳ  ይሆናል፡፡ በሽታው ከተስፋፋ ቢጫው  ጠባሳ እየበዛ ይመጣና ቢጫ ጠባሳ  የነበሩት ቅጠሎች ወደ ጥቁር ጠባሳ ይቀየራሉ፡

የሚከሰቱበት ሁኔታ

በሽታ አምጪ ተህዋስያኑ በዘር ውስጥ ወይም በተክል ውስጥ ይቆያሉ  ተህዋስያኑ በንፋስ፣ ዝናብ እና በእርሻ መሳሪዎች ይዛመታሉ የበዛ ዩሪያ ኮምፐስት ፣ ያለጊዜ መዝራት እና ያለጊዜ ጎመን ራስ  መንቀል ለክስተቱ መጨመር አስተዋጽኦ አላቸው፡፡

መከላከያ ዘዴ ጤናማ ዘር መጠቀም ወይም ዘሩን ለ5 ደቂቃዎች በ55ዲሴ ውሃ  ውስጥ ማስቀመጥ፣ ነፍሳቶችን ማስወገድ እና ቅጠሎችን ከጠባሳ መከላከል፣  ፀረ-አረምን መጠቀም፡፡ ኬሚካል ዘዴ ዘሩን በ100 ሚግ/ሊ Streptocycline ለ30 ደቂቀዎች በመንከር  መከላከል ይቻላል፡፡ ተክሉን ከተከልን በኋላና ጎመን ራሶቹ ከበቀሉ  በኋላ ሁለት ዙር Copper oxychloride + Streptomycin 100 ppm  መርጨት፡፡

ምልክቶች የታችኛው ቅጠልና ግንድ ለስላሳና ብስባሽ ይሆናሉ፣ የታመመው የተክሉ የላይኛው ክፍል አረንጓዴ ሆኖ ይጠወልጋል፣  እና ሽታም ይኖረዋል ፡፡   የሚከሰትበት ሁኔታ በሽታ አምጪ ተህዋስያኑ በተክሉ ላይ ወይም በአፈሩ ላይ ይኖራሉ፣  በተጨማሪም በዝንቦች እጭ ላይ እና በክረምት ወቅት ይኖራሉ ፡፡   መከላከያ ዘዴ በተበከለው ተክል አካባቢ ባቄላ መትከል፣ ተህዋስያኑ በደረቅ ሁኔታ ደካማ ስለሆኑ በቂ ተፋሰስ እና በቂ የአየር  ዝውውር እንዲኖር ማድረግ ፣ እውቅና ያላቸውን ኬሚካሎች መጠቀም፡፡