ተስማሚ አካባቢ


በአገሪቱ ደጋማ ክፍሎች ማለትም ከ1600-2800 ሜትር ከፍታ ድረስ የሚመረት ቢሆንም በተለይ ከ2300-2800 ሜትር ከፍታ ባላቸው ቦታዎች የበለጠ ምርታማ ነው፡፡ ከ18-31 ዲግሪ ሴንቲ ግሪድ የሙቀት መጠን ተስማሚው ሲሆን በተፈጥሮው ውርጭን የመቋቋም ባህሪይ አለው፡፡  ሆኖም ግን ረዥም የፀሃይ ብርሃን (16-20 ሰዓት) ይፈልጋል፡፡ የሚያስፈልገው ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ450-500 ሚ.ሜ. ሲሆን የዝናብ እጥረት ካጋጠመው  እድገቱን በማፋጠን ምርታማነቱን ይቀንሳል፡፡

በማንኛውም ከአረም የፀዳ የአፈር ዓይነት ላይ ሊመረት ይችላል፡፡ እርጥበትን ማቆየት የሚችልና ቀለል ያለ አፈር የበለጠ ይስማማዋል፡፡ ዉሃ በሚያቁር አፈርና በጣም መረሬ በሆነ አፈር እድገቱ ሊቀንስ ይችላል፡፡ በጣም አሸዋማ አፈርም አይስማማውም፡፡