ተስማሚ አካባቢ


ሰሊጥ ሞቃታማ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች የሚመረት የቅባት ሰብል ነው፡፡ ከባህር ጠለል በላይ እስከ 125ዐ ሜ ከፍታ እና ከ5ዐዐ እስከ 8ዐዐ ሚ.ሜ ዝናብ የሚያገኙ ቦታዎች በይበልጥ ይስማሙታል፡፡
የአፈር ዓይነት
ሰሊጥ በተለያዩ የአፈር ዓይነቶች ላይ መልማት ቢችልም በተለይም ውኃ በቀላሉ የሚያሰርግ ጨዋማ ያልሆነ አፈር ይስማማዋል፡፡ ውኃ ይዞ የሚቆይ አፈር ለሰሊጥ ዕድገት ምቹ አይደለም፡፡