overview


ሳይንሳዊ ስያሜ : Solanum lycopersicum .L

በተለምዶ  አጠራር : ቶማቶ (እንግሊዝኛ)፣ ቶማቴ (ስፔን፣ ፈረንሳይ)፣

                             ቶማቲ (ምዕራብ አፍሪካ)፣ ቲማቲም(አማርኛ)

የተገኘበት ሀገር: ደቡብ አሜሪካ ግዛቶች

  • ይህ ዝርያ የተገኘው በደቡብ አሜሪካ ሲሆን በደቡብ አሜሪካ የስፔን ቅኝ ግዥን ተከትሎ በመላው አለም ተሰራጨ፡፡
  • ቲማቲምን በተለያየ መልኩ እንጠቀመዋለን፡፡ እንደ ሶስ፣ ሰላጣ እና በፈሳሽ መልክ ልንመገበው እንችላለን፡፡ ለጤንነት በጣም ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ ፍሬ ነው፡፡
  • ቲማቲም በአብዛኛው ከ1-3 ሜትር ርዝመት ያድጋል፡፡ አማካኝ የቲማቲም ክብደት በግምት 100 ግራም ይመዝናል፡፡
  • በአጠቃላይ ቲማቲም ሊሶፌን፣ ካሮቲን፣ አንቶሳይኒን እና ሌሎችን ፀረ ወክሳጆችን ያመርታል፡፡ ሊሶፌን አንዱና ይበልጡን ተፈጥሮአዊ ሀይል የያዘ ፀረ ወክሳጅ ነው፡፡ ቆዳን ጎጂ ከሆነው ከዩቪ(አልትራ ቫዮሌት) ጨረር የመከላከልን አቅም የተሻለ ማድረጉም ተረጋግጧል፡፡