አመራረት


  • መሬቱን በደምብ በማረስ ለዘር ዝግጁ ማድረግ
  • ከመዘራቱ ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት ቀደም ብሎ በማሳው ዙርያ የናፒር ሣር ቁራጮችን በ6ዐ ሣ.ሜ እያራራቁ በ2-3 ረድፍ መዝራት
  • በቆሎውን ለአካባቢው በወጣው የዘርና የማዳበሪያ መጠን መዝራት
  • ከመጀመሪያው ሽልሻሎ በኋላ በየሁለት መስመር በቆሎ መካከል አንድ መስመር ዴዝሞዲየም መዝራት
  • ዴዝሞዲየመና ናፒር ሣሮችን በቆሎው በቂ ቅጠል ሲያወጣና አስተማማኝ የዕድገት ደረጀ ላይ ሲደርስ ጠብቆ በማጨድ ለከብቶች መኖ መጠቀም፡፡