አስተራረስ


የሽንኩርት ቡቃያ በቀን ርዝመት ይወሰናል ፣ የሽንኩርት ራሶች ማደግ የሚጀምሩት  ብርሃን ያገኙበት የሰአታት ርዘመት ይወሰናል።  የቀን ሰዓታት ብዛት ከትንሹ የብርሃን  ሰአት ርዝመት መስፈረት ሲበልጥ ነው። አብዛኛው የአውሮፓ በቀል ሽንኩርቶች  “የረዥም ቀን ሽንኩርቶች” ተብለው ይጠራሉ።

የሽንኩርት ራሶች ከ 14 ሰዓታት በኋላ ወይም የቀን ብርሃን ካገኙ በኋላ ማደግ  ይጀምራሉ። የደቡብ አውሮፓ እና የሰሜን አፍሪካ ዝርያዎች ብዙውን ጊዜ  “የመካከለኛ ቀን” ሽንኩርት ዓይነቶች በመባል ይታወቃሉ፣ ይህም የሽንኩርት ራሶች  ማደግ እንዲጀምሩ ለማነሳሳት ከ12-13 ሰአታት የቀን ብርሃን ብቻ ያስፈልጋቸዋል  በመጨረሻም “የአጭር ቀን” ሽንኩርት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት መዘራት የጀመረ  ሲሆን፣ በበልግ እና በመለስተኛ የክረምት ወቅት ተተክሎ በፀደይ መጀመሪያ ላይ  የሽንኩርት ራስ ማብቀል ሲጀምር ከ 11-12 ሰአታት ብቻ የቀን ብርሃን ይፈልጋል።  ሽንኩርት ሲከተፍ አንዳንድ ኬሚካሎችን በመልቀቅ የአይንን የእንባ እጢ  የማስቆጣት ከ አይን እንባ እንዲወጣ ያደርጋል።

. ትልቅ የሽንኩርት እርሻ (ግራ)
የሽንኩርት አበባዎች ክምችት(ቀኝ)

የሽንኩርት ተክል እድገቱ ቀስ ያለና ከአረም ጋር ሲነፃፀር ደካማ የሆነ  ፉክክር ያሳያል። በእርጥበት ለውጥ በቀላሉ ይጠቃል። ተክሉ በቁጥር  የተወሰነ ስር ስላለው ትክክለኛ የሆነ የማዳበሪያ እና የመስኖ ቁጥጥር  ይሻል። ይሄ የእድገት ደረጃ 37 ቀናት ይፈጃል። ከታች ያለው ምስል  ይሄንን ደረጃዎች ያሳያል።

መንጠቆ መሳይ ቅጠል (ግራ)እና ሶስት እውነተኛ ቅጠል የሚያሳዩበት ደረጃ (ቀኝ)

. በቀሌ

ሽንኩርት ረቂቅ ሆኖ የተሰራ ከጠንካራ መሰረት 2-3 ሴ.ሜ ጥልቀት  ያለው የዘር መደብ ያስፈልገዋል። የመሬቱ ዝግጅት በአፈሩ አይነትና  ቀድሞ በተዘራው የሰብል አይነት ይወሰናል። ጥብቅብቅ ባሉ አፈሮች ላይ  በቅድሚያ አፈሩን መሰንጠቅ እና ማረስ አስፈላጊ ይሆናል።

ዘር

የደረሰ የሽንኩርት ዘር ጥቁርና ማእዘናዊ ነው። አንድ የዘር ኪሎ ቁጥሩ ቢለያይም  280,000-320,000 ዘሮችን ይይዛል። የመስክ ዘር ማብዛት 80% አመርቂ  ውጤትን ያስመዘግባል። ሽንኩርት በመቀመጥ ብዛት የዘር ማብዛት አቅሙ  በፍጥነት ስለሚዳከም አገልግሎት ላይ ከመዋሉ በፊት መመርመር ይኖርበታል።