ሀ. ችግኝ የማፍላት ቴክኖሎጂ
1) ችግኝ ማፍላት
በአጠቃላይ ቲማቲምን የምንተክለው ችግኝ አፍልተን ከዛም ቦታ ቀይረን በመትከል ነው፡፡ ምክንያቱም የተሻለ ውጤት የሚገኘው ችግኝ በማፍያ ውስጥ ስናሳድገው ነው፡፡
ጥቅሙ ① በመስክ ላይ ከመትከላችን በፊት ጤናማ ችግኝ መምረጥ ያስችለናል ፡፡
② የአተካከል ርቀቱ በመዝራት ከምንተክለው በተሻለ ተስተካክሎ በተመሳሳይ ርቀት እንድንተክል ያስችለናል፡፡
ሀ. ችግኝ የማፍላት ቴክኖሎጂ
– መዝሪያ አፈር : ከቬርሙላይት(3) ፣ ፔርላይት(2) ፣ ፒተሞስ(1) የተደባለቀ መሆን አለበት
2) የችግኝ ማፍያ ማዘጋጀት
– አረም ከዘር ማፍያ ውስጥ ማስወገድ
– አፈር አሲዳማነት pH & EC : pH5.5 እና 7.5 / EC 1.5~2.0 dS/m
(culture solution)
– ዘር የሚዘራበት ሰሀን የሙቀት መጠን : በቀን 25ዲሴ፣ በማታ ከ23-25 ዲሴ፤ አየር እርጥበት 80 በመቶ መሆን አለበት
ችግኝ ማፍያ ቦታ ማዘጋጀት
Soil pH & EC : pH 5.8 ~ 6.0 / EC 0.5 ~0.8 (ms/cm)v
ከ28-30ዲሴ ጥሩ የመብቀያ የአየር ሙቀት መጠን ነው
ከበቀለ በኋላ የአየር ሙቀት መጠኑን ከ20-25 ዲሴ መጠበቅ
ተክሉን በቀን ከ1-2 ጊዜ ውሃ ማጠጣት
ለችግኙ አየር ማናፈስ አስፈላጊ ነው
ሐ. መስክ ማዘጋጀት
መስኩን ማረስ በአዲስ ሰብል ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነው
ጥቅሙ
መ. መደብመሥራት
ጠቅላላ የማዳበሪያ ብዛት(ቶ /1ሄክታር)
የቲማቲም መደብ ከመስራታችን በፊት መደበኛ ማዳበሪያና ፍግ በአፈሩ ላይ ማድረግ፣üበመደብ ላይ ሁለት መስመር አስተራረስ የመሬቱን እርጥበት ለመጠበቅ ይረዳል፣ አንድ መስመር አስተራረስ ውሃ በአፈሩ ላይ ጠፈፍ እንዲል ጥሩ ነው፡፡
ሠ. ንቅለተከላ (ተክል ማጓዝ)
ከጎን የሚበቅሉ ትናንሽ ቅርንጫፎች ተወግደው አንድ ዋና ግንድ ብቻ ይቀራል፣
ፍሬዎች የሚበቅሉት በዋናው ግንድ ዙሪያ ነው፣
ትናንሽ ቅርንጫፎችን መቁረጥ የፍሬውን መጠንና ጥራት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
ለ. መቸከል
የቲማቲምን ተክል ዕድገትና የተክሉን ክብደት ለመደገፍ ይረዳ ዘንድ ችካል አስፈላጊ ነው፣
ስንደዶ፣ ፕላስቲክ ገመድ፣የዕፅዋት ማሰሪያ ገመድ ወይም ሌላ ነገሮች ለችካል መጠቀም ይቻላል፡፡
ጥቅሙ: ① የፍሬው ቅርጽ ይጨምራል
② የፍሬውን መበስበስ ይቀንሳል
③ ውሃ ለማጠጣትና ምርት ለመሰብሰብ ቀላል ይሆናል
ሐ. አጠቃላይአያያዝ
ውሃ ማጠጣት
– ቦታ ቀይረን ከተከልን በኋላ በቂ የውሃ መጠን ማጠጣት ያስፈልጋል፣
– በአብዛኛው ከ4-5 ባሉት ቀናት ውስጥ ተክሉን ውሃ ማጠጣት፣
– በአፈር ውስጥ የበዛ እርጥበት ካለ የቲማቲሙ ጥራት መጥፎ ይሆናል፡፡
አፈር አያያዝ
-አፈሩ በጣም እርጥበታማ ከሆነ ቲማቲሙን በሽታ ሊይዘው ይችላል፣
-የተሻለ የሚሆነው ውሃ ማስረግ የሚችል ጥሩ ተፈጥሮአዊ አፈር መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፣
– አፈሩን በጥቁር ፕላስቲክ በመሸፈን አረምን መከላከል፡፡üአተካከል ምክር
የተክሉን ችግኝ በጣም በጥልቀትና፣ ተገቢ ጥልቀት በሌለው ሁኔታ አለመትከል፣
-አጓጉዘን ከተከልን በኋላ ተክሉ በፍጥነት ስር እንዲያወጣ ውሃ ማጠጣት አስፈላጊ ነው፡፡