ችግኝ የማፍላት ቴክኖሎጂ
5-1-1. ችግኝ ማፍላትና አያያዝ
(ሀ) ዘር መበከሉን ወይንም አለመበከሉን ማረጋገጥ ከብክለት ካልፀዳ ለአንድ ሰዓት 10ፐርሰንት ትሪሶዲየም ፎስፌት ውህድ ውስጥ ዘሩን መዘፍዘፍ
(ለ) ከተክል ማጓዝ በፊት ችግኝ ከ40-45 ቀናት ውስጥ ማፍላት እያንዳንዱ የበርበሬ ዘር በ1/4ኛ ኢንች ጥልቀት በማፊያ ውስጥ መዝራት
ከዘራን በኋላ ውሃ ማጠጣት፣ አፈሩ እርጥበቱን ይዞ እንዲቆይ ማድረግ፣ በቀን በቀንም የአፈሩን እርጥበት መፈተሽ
(ሐ) የተዘራው ዘር መጠን ወደ መደበኛው ከ2.0-3.2 ግንድ ይቀየራል(ግንድ ውፍረት 6.6 per)v
ችግኝ ማፊያ ሳጥኖች
– ችግኝ ማፊያ አፈር፡ ቬርሚኩላይት(3)፣ፔሪላይት(2) እና ፒትሞስ(1) ጋር መደባለቅ፣
-ዘር ከምናፈላበት ሳጥን ውስጥ አረምን ማስወገድ፣
– አፈር አሲዳማነት (ፒኤች እና ኢሲ)፤ ፒኤች 5.5 እና 7.5/ኢሲ 1.5-2.0 ዲኤስ/ኤም (ርባተ ዋስያን ውህድ)፣
– የችግኝ ማፍያ ሳጥን አየር ጠባይ፡ በቀን 25ዲሴ፣ በማታ ከ23-25ዲሴ፤ አየር እርጥበት 80ፐርሰንት መሆን አለበት፡፡