ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት


በሀገራችን ቆላማ አካባቢዎች ያሉንን የተፈጥሮ ፀጋዎችን (ውሃ፣ ለም አፈር፣ በቂ የፀሐይ ብርሃን፣ የሰው ጉልበት፣ ወዘተ) በመጠቀም ስንዴን በስፋት ብናመርት የራሳችንን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥም አልፈን ወደ ጎረቤት ሀገሮች በመላክ የውጭ ምንዛሬን ማግጀት እንችላለን፡፡ የስንዴ ገለባውን ለእንሰሳት መኖነት በመጠቀም የሀገሪቱን የሥጋና ወተት ምርትን ማሻሻል ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ስንዴን በመስኖ በማምረት በቆላማው የሀገራችን አካባቢ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ማህበረሰቡን በተለይ ደግሞ ሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ስለሚቻል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

የሰብሉን አዋጪነት  ከቦታ ቦታ የወጪና ገቢ ዋጋዎች ስለሚለያዩ ወጥ የሆነ ትርፋማነትን ማስቀመጥ ስለማይቻል በዕዝል 1 መሠረት ወጪዎችን (የቤተሰብ ጉልበት፣ በደቦና በጅጊ የሚወጡ ወጪዎችን በጉልበት ሠራተኛ በመተመን በማካተት እንዲሁም ገቢን ከእህልና ከገለባ በአካቢባ ዋጋ በማስላት) ትርፋማነቱን ማወቅ ይቻላል፡፡ ሆኖም አርሶ/አርብቶ አደሩ ለሚያወጣው አንድ ብር ሁለት ብር እና በላይ ገቢ ካላገኛ አዋጪ ነው ማለት አይቻልም፡፡

ዕዝል 1፡የኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ስሌት