የመስኖ አጠቃቀም


የወይን ተክል በአብዛኛው የስሩ አካል ከ2ዐ-6ዐ ሣ.ሜ ጥልቀት ወስጥ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በበጋ በተለይ በማበቢያና ፍሬ በመያዣው ጊዜ የወይን ማሳ የመስኖ ውሃ ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ወቅት በየሣምንቱ ማሳው ውሃ ማግኘት አለበት፡፡ የመስኖ ውሃ ችግር በሌለበት አካባቢ ከገረዛ ጀምሮ የፍሬው ቀለም እስከሚወይብበት ድረስ በየሣምንቱ ማሳውን ውሃ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡