የማሣ ዝግጅትና ዘር መዝራት


ቦቆሎ ከፍተኛ ምርት እንዲሰጥ ውሃ የማይተኛበትና ለም አፈር ያስፈልገዋል፡፡ ዘር ከመዘራቱ በፊት ከ2-3 ጊዜ በሚገባ ማረስ አፈሩን ለዘር አመቺ ደርገዋል፡፡ የለያዩ አረሞችን ለመከላከልና ብስባሾችን ለመቅበርም ያግዛል፡፡ ማሳው በሚቆረስበት ጊዜ የመሬት መሸርሸርን ለመከላከልና የአፈር እጥበትን ለመጠበቅ ተዳፋት መሬቶችን አግድም ማረስ ያስፈልጋል፡፡ የዘር ወቅት እንደአካበቢው የሚለያይ ስለሆነ በአካባቢው የዝናብ ወቅት መሠረት መሬቱ ዘር ለማብቀል በቂ ውሃ ሲይዝ መዝራት አስፈላጊ ነው፡፡ በደንብ ርሶ ለዘር የተዘጋጀ መሬት በአማካይ 25-3ዐ ኪ.ግ. ዘር ያስፈልገዋል፡፡ ዘሩ በመስመር መዘራት አለበት፡፡ በመስመሮች መካከል 75 ሴ.ሜ ስፋት ሊኖር ይገባል፡፡ መስመር በተዘሩ ተክሎች መካከል ደግሞ 3ዐ ሴ.ሜ ስፋት መኖር ይገባዋል፡፡ በተጨማሪ አጭርና ቀጥ ያለ ቅጠል ያላቸውን ዝርያዎች በ25 ሴ.ሜ አራርቆ መዝራት ይቻላል፡፡