የማዳበሪያ  አጠቃቀም


የአኩሪ አተር ተክል ከሌሎች የጥራጥሬ፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች የበለጠ መጠን ናይትሮጂን፣ ፎስፈረስ፣ፖታሽየም፣ማግኒዚየምና ካልሲየም ንጥረ ነገር ይፈልጋል፡፡ አኩሪ አተር 1 ቶን የዘር ምርት በሄክታር ለመስጠት ከአፈር ውስጥ 80 ኪ.ግ ናይትሮጂን በሄክታር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ 100 ከ.ግ ዳፕ በሄክታር በዘር ወቅት ዘሩ ከመዘራቱ በፊት መበተንና ከአፈር ጋር ማደባለቅ ያስፈልጋል፡፡ ኬሚካል ማዳበሪያ መግዛት የማይችል አምራች ፍግ ወይንም ኮምፖስት አዘጋጂቶ ማሳውን ለዘር ከማዘጋጀቱ በፊት መበተን ጥሩ ምርት ያስገኛል፡፡ መጨመር ያለበት ፍግ ወይንም ኮምፖስት እንደ አፈሩ ለምነት  ኬሚካል ማዳበሪያ አደባልቆ የመጠቀም ፍላጎት የሚወሰን ሲሆን  ኬሚካል ማዳበሪያ መጠቀም የማይፈልግ ገበሬ ከ6-10 ቶን ፍግ ወይም ኮምፖስት በሄክታር በመጨመር ጥሩ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡

አሰባጥሮ መዝራት

ሁለት መስመር በቆሎና ሁለት መስመር አኩሪ አተር በማፈራረቅ መዝራት ጥሩ ምርት ያስገኛል፡፡