የማዳበሪያ አጠቃቀም


በሄክታር የሚያስፈልገው የማዳበሪያ መጠን እንደአካባቢውና የአፈሩ ለምነት ይለያያል፡፡ ስለሆነም ማዳበሪያ ከመጠቀማችን በፊት ለአካባቢው የሚያስፈልገውን የማዳበሪያ ዓይነትና መጠን በአቅራቢያው ካለ የግብርና ባለሙያ ጠይቆ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉት ማዳበሪያዎች ዩሪያና ዳፕ ናቸው፡፡


የማዳበሪያዎችን ዝርዝር የአጠቃቀም መጠን ከሠንጠረዡ ይመልከቱ፡

በተለያዩ አካባቢዎች የተተመነውና በሥራ ላይ የዋለው የማዳበሪያ መጠን ፺ዳፕና ዩሪያ፻

ማሳሰቢያ፣ ለአካባቢው የተተመነው የዩሪያ መጠን መጨመር ያለበት በቺኩል መጠን ለሁለት ተከፍሎ ነው፡፡ የመጀመሪያው በዘር ወቅት መዘራት ያለበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የበቆሎው ቁመት ከጉልበት ከፍቆ በላይ ሲደረስ ፺በአማካይ 45 ቀናት፻ ነው፡፡ በተጨማሪም የአፈር ለምነትን ለመጠበቅና ፍግና ብስባሽን እንደአማራጭ መጠቀም ይቻላል፡፡