የቡና ምቀሣ ከመካሄዱ በፊት ሁለት መሠረታዊ ዕውቀቶች ያስፈልጉናል፡፡ እቺነሱም የቡናውን አስተዳደግና አቋም እቺና
ለቡና ዕድገት ምግብ አዘጋጅና ምግቡን የሚጠቀሙት የቡናው አካሎች ግንኙነት ማወቅ ናቸው፡፡
ቡና አነስተኛ ዛፍ ሲሆን ወደላይ የሚያድገው አካሉ ዋነኛው ነው፡፡ ከዚሁ ላይ የሚነሱት ተቀጥላ ግንዶች የቡናውን ግንድ
ቁጥር ለመጨመርና ቡናውን ለማደስ የተዘጋጁ የቡናው ዓይነተኛ አካሎች ናቸው፡፡ ግንዱ ከጎን የሚያወጣቸው
የመጀመሪያ ቅርንጫፍ፣ ከዚሁ ላይ የሚነሱት ደግሞ ሁለተኛ ቅርንጫፎችና ከሁለተኛ ቅርንጫፍ ላይ የሚነሱ ሶስተኛ
ቅርንጫፎች ይኖሩቆል፡፡ አንድ የመጀመሪያ ቅርንጫፍ ምን ጊዜም ከመጀመሪያው የአንጓ ዓይን በቆች ከተቆረጠ መልሶ
አያቆጠቁጥም፡፡ ነገር ግን ሁለተኛና ሶስተኛ ቅርንጫፎች ተቆርጠው ቢወገዱም ሌላ መልሶ የማውጣት ባህርይ አላቸው፡፡
ምግብ በዋነኛነት የሚያዘጋጀው የቡና ተክል ክፍል ቅጠሉ ሲሆን ለጋ ቅጠሎች፣ ግንዶች፣ የሥር ጫፎችና በተለይም
ፍሬው ከፍተኛ የምግብ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ምግብ ሁልጊዜ ከምንጩ ወደ ተጠቃሚው በመፍሰስ ግንኙነት ይኖራል፡፡
የምግብ ምንጩ ቅጠሉ በአንድ ጊዜ ለሁለት ነገሮች ያገለግላል፡፡ እቺነሱም ቡናው ያፈራውን ፍሬ መመገብና
ለሚቀጥለው ዓመት ምርት የሚገኝበትን ግንድም ሆነ ቅርንጫፎች ወደ ላይና ወደ ጎን ማሳደግ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ቡናው ከፍተኛ ምርት ይዞ ቅጠሉ ግን ትንሽ ከሆነ የምግብ ምንጩ ሙሉ በሙሉ ወደ ፍሬው ስለሚፈስ ምርት ከተለቀመ
በኋላ ቡናው ሊዳከም ይችላል፡፡ ስለሆነም ለሚቀጥለው ዓመት በቂ የተከማቸ ምግብ ስለማይኖር ምርት ላይገኝ
ይችላል፡፡ በተለምዶ ቡና አንድ ዓመት ከሠጠ በሚቀጥለው ዓመት አይሠጥም የሚባለው የቅጠልና የፍሬን
ተመጣጣኝነት ባለመጠበቅ የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር በገረዛና በሌሎችም የአያያዝ ዘዴዎች ለምሳሌ እንደ
ምርት አያያዙ ማዳበሪያ መጨመርና ጥላን መጠቀም፻ ማሻሻል ይቻላል፡፡
ቡና የሚገረዝባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
የቅጥያ ማንሳት ሥራ፡- ከዋናው ግንድ ላይ የሚነሱ ቁጥራቸው የበዙ ቅጥያዎችን ማስወገድ