በቀይ እሸት ቡና ለቀማ ወቅት ድብልቅ ለቀማ ማከናወን
ቀይ እሸት ቡናን ካልበሰለ፣ በመጠኑ ከደረቀ፣ መሬት ላይ ከወዳደቀ እና ብስለቱ ካለፈበት ቡና ጋር አደባልቆ መጠቀም ፡፡ ቀይ እሸት ቡናን ከባዕዳን ነገሮች /የዋንዛ ፍሬና ቅጠላ ቅጠል/ ጋር አብሮ መጠቀም፡፡
ቡና በሚፈለፈልበት ወይንም በሚታጀልበት ወቅት
በመጠኑ እና በመብሰል ደረጃው የተደበላለቀ ቀይ እሸት ቡና አንድ ወጥ የሆነ የቡኬት ጊዜ ስለማይኖረው የስተካከለ ቡኬት እንዳይኖርና ቡናው ሲፈለፈል በቀላሉ እንዲሰባበር ያደርጋል፡፡ በተደበላለቀ የቡና ለቀማ ወቅት አነስተኛ መጠን ያላቸው ቡናዎች ሳይፈለፈሉ ሊያልፉ ስለሚችሉ ይህን ዓይነት ለቀማን ማስወገድ፣ ለቀማው ከተካሄደ ደግሞ በየደረጃው መለያየት ያስፈልጋል፡፡ ንፅህናውን ያልጠበቀ አካባቢ እና የቡና ማጀያ ገንዳ በቡና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃን ለማጀያ መጠቀም ለቡና ጥራት መጓደል መንስዔ ይሆናል፡፡ የቡኬት ሰዓት መርዘም ወይንም ማጠር፣ ከፈርመንቴሽን በፊት የሚደረግ እጥበትና የበሰበሰ ቡና መኖር የቡናን ጥራት ከሚቀንሱ ምክንያቶች ውስጥ ይመደባሉ፡፡
በቡና ማድረቂያ ወቅት
የመጀመሪያ ደረጃ የቡና አደራረቅን በትክክል ለመፈፀም እና ቡናን ለከፍተኛ የፀሐይ ሙቀት ረዘም ላለ ጊዜ ማጋለጥ የቡናን የላይኛውን ሽፋን መሰንጠቅና የጥራት ጉድለትን ያስከትላል፡፡ በደረቅ ቡና ዝግጅት ወቅት ቡናን በጆንያ ወይንም በሌሎች ዕቃዎች ማፈን፣ ትክክለኛ የርጥበት መጠን ያለመጠቀምና በማድረቂያ ላይ የቡና ጥልቀት ከሚገባው በላይ መሆን ለቡና ጣዕምና ጥራት መቀነስ መንስዔ ናቸው፡፡
በቡና ክምችት ወቅት
ደረጃውን ያልጠበቀ መጋዘን አሰራር፣ የማከማቻ ዕቃዎች ንፁህ ያለመሆን፣ ሽታ ያለው የማከማቻ ዕቃ መጠቀም እና ቡናን ረዘም ላለ ጊዜ በመጋዘን ውስጥ ማከማቸት የቡና ጣዕምና ጥራት ይቀንሳሉ፡፡
ጣዕምና ጥራት ላለው ቡና የሚደረግ ጥንቃቄ
በለቀማ ወቅት
በሚፈለፈልበት ወቅት
በሚታጀልበት እቺና በሚቆጠብበት ወቅት
በሚደርቅበት ወቅት