የተሻሻሉ ዝርያዎች


እስከ አሁን ሰባት የአበሻና አራት የአርጀንቲና ጎመንዘር ዝርያዎች ለምርት የተለቀቁ ቢሆንም፤ በአሁን ወቅት ጥቂቶቹ ብቻ በመመረት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ የአበሻ ጎመንዘር ዝርያዎች ዘግይተው የሚደርሱና የዘር ምርታቸው ከአርጀንቲና ጎመንዘር የሚበልጥ ቢሆንም የዘይት ይዘታቸው ግን አናሳ ነው (ሰንጠረዥ 1)፡፡