የአመራረት  ዘዴዎች


የማሳ ዝግጅት

የተሻለ ምርት ለማግኘት ሦስት ጊዜ ታርሶ በደንብ የለሰለሰና ከአረም የፀዳ ማሳ ያስፈልገዋል፡፡

የዘር ወቅት

 ከፍታቸው ከ2000 ሜትር በላይ በሆኑ አካባቢዎች ለሚመረት ኑግ (አባት ኑግ) ከሰኔ ወር አጋማሽ እስከ ሐምሌ መጀመሪያ ድረስ ያለው ጊዜ ተመራጭ የመዝሪያ ወቅት ሲሆን ከፍታቸው ከ 2000 ሜትር በታች ለሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ከሰኔ አጋማሽ እስከ ሰኔ መጨረሻ ያለው ጊዜ ተስማሚ የዘር ወቅት ነው፡፡

የዘር መጠን

የኑግ የዘር መጠን እንደሚዘራበት ወቅት ይለያያል፡፡ ዘግይቶ በሚዘራበት ወቅት ከ 5-10 ኪ.ግ በሔክታር ቀደም ብሎ በሚዘራበት ውቅት ደግሞ ከ10-15 ኪ.ግ በሔክታር ዘር መጠቀም ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ግን ኑግ በመስመር ሲዘራ 10 ኪ.ግ በሔክታር በብተና ከሆነ ደግሞ 12 ኪ.ግ በሔክታር የዘር መጠን መጠቀም ተመራጭ ይሆናል፡፡