የአመራረት ዘዴ


ለውዝን ለማምረት የአፈሩ ዓይነት ወሳኝ ነው፡፡ የለውዝ ፍሬ መሬት ወስጥ የሚፈጠር በመሆኑ ፍሬው የሚፈጠርበት የተክሉ አካል በቀላሉ ወደ አፈር መግባት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ፍሬ ከመያዙ በፊት ይመክናል፡፡ ስለሆነም ለውዝ የሚመረትበትን መሬት ከአበባ በፊት በመኮትኮት ማለስለስ አስፈላጊ ነው፡፡ ጥሩ ምርት ለማግኘት ቀላል አፈር እና የተስተካከለ ስርጭት ያለው  ከ6ዐዐ እስከ 9ዐዐ ሚ.ሜ የዝናብ መጠን የሚያገኙ አካባቢዎች ይመረጣሉ፡፡ በመስኖ ጥናት መሠረት ከ1ዐ-15 ሣ.ሜ. ጥልቀት በየ15 ቀናት ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡

ማሣ ማዘጋጀት

ለውዝ በቡቃያነቱ አዝጋሚ ዕድገት ስላለው ከአረም ጋር የመፎካከር አቅሙ ደካማ ነው፡፡ ስለሆነም የለወዝ ማሣ ከአረም የፀዳ መሆን አለበት፡፡ ማሳውን እንደ አፈሩ ዓይነት ከ2-3 ጊዜ ማረስ ያስፈልጋል፡፡