የአስተራረስ ሁኔታ


የአየር ጠባይ

ለቡቃያው ምቹ የአየር ጠባይ ከ18-35ዲሴ ከቡቃያው በኋላ ለጎመን  ዕድገት ምቹ የአየር ጠባይ ከ15-20 ዲሴ ነው፡፡ የአየር ጠባዩ  ካልተስተካከለ ጎመኑ የተፈጥሮ መዛባት ይኖረዋል፡፡ የአየር ጠባይ ከ0ዲሴ በታችና ከ25ዲሴ በላይ ያለበት ሁኔታ ማስወገድ አለብን፡፡  ለማበብም ከ10ዲሴ በታች እና ከ5-6 ሳምንታትን ይፈልጋል፡፡

አፈር

ጥቅል ጎመን በተለያዩ ደረጃ ላይ ያሉ አፈሮች ላይ ይበቅላል፡፡ ነገር ግን  አሲዳማ የሆነ አፈር አይስማማውም፡፡ የጥቅል ጎመን ለማደግ ምቹ  የአፈር አሲዳማነት መጠን ፒ.ኤች 6.0-6.5 ነው፡፡

ብርሃን

ለጥቅል ጎመን ሙሉ የፀሀይ ብርሃን ተመራጭ ነው፡፡ ነገር ግን የጥቅል  ጎመን የቀዝቃዛ አየር ሰብል ስለሆነ ቀዝቃዛ አየርን ይፈልጋል፡፡ በቀን  ክፍለ ጊዜም የተወሰነ ጥላን መቋቋም ይችላል፡፡

ማዳበሪያ

ማዳበሪያን ከመጠቀማችን በፊት በአፈር ውስጥ ያለውን ንጥረነገር  ማጣራት አለብን፡፡ የጥቅል ጎመንን ለማረስ መደበኛ መጠን N-P-K  200፤125፤150 ኪግ/በሄክ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ተሞክሮ 200 ዳፕ እና 100 ዩሪያ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከመትከላችን በፊት በሄክታር 50ኪግ ፎስፈረስ እና ከ120-180 ኪግ ፖታሺየም ብንጠቀም  ለጎመኑ ዕድገት ጥሩ ነው