የአስተራረስ  ሁኔታ


የአየርሙቀት

  • ቲማቲም ቀዝቃዛና ደረቅ የአየር ፀባይን ይፈልጋል
  • ለማደግ ምቹ የአየር ፀባይ : 21~24ዲሴ
  • ከ10ዲሴ በታችና ከ38ዲሴ በላይ ከሆነ የተክሉ ህብረህዋሳት ይጎዳሉ

     አፈር

  • ቲማቲም በይበልጥ የተሟላ የውሃ ማቆር አቅም ባላቸው የማዕድን አፈር ላይ      በጥሩ ሁኔታ ያድጋል፣ እና አፈሩም ከጨው የፀዳ መሆን አለበት፣ለጤናማ ተክል የአፈር ጥልቀት ከ15-20ሴሜ መሆን አለበት፣
  • ቲማቲም በአፈር አሲዳማነት መጠን በ pH 5.5 – 6.8 ባለ አፈር ላይ በጥሩ     ሁኔታ ያድጋል፡፡

ተክል አጓጉዘን ከመትከላች ከ2-3 ሳምንት በፊት በ1ሄክታር መሬት ላይ ከ17-21-17(N-P-K) የተውጣጣ ማዳበሪያ 1.45ቶን፣ ኖራ 1.21ቶን፣ ፍግ 30.3ቶን በመሬቱ ላይ በማድረግ ማረስ፡፡

     ውሃና እርጥበት

የውሃ እጥረት የተክሉን ፍሬ እንዲረግፍ ያደርገዋል፡፡ ይሁንና በጣም ከባድ  ዝናብ ከሆነና እርጥበትም በጣም ከፍተኛ ከሆነ ፍሬው ይበሰብሳል፡፡