የአየር ጠባይ
– ለቡቃያ ምቹ የአየር ጠባይ፡ ከ15-27ዲሴ
– ለማደግ ምቹ የአየር ጠባይ፡ ከ18-20ዲሴ
ክፍልፋይ ኩርት መለያያ ጊዜ፡ በ30 ቀናቶች ውስጥ ከ5-10ዲሴ በሆነበት ጊዜ ውስጥ
ኩርት ዕድገት፡ ከ18-20ዲሴ
– ዕድገት የሚዛነፍበት የአየር ጠባይ፡ ከ10ዲሴ በታች እና ከ25ዲሴ በላይ በሆነ ጊዜ
አፈር
– በደንብ የተንጣፈፈ ቀይ አፈር ወይም ሸክላማ አፈር ብዙ ማዳበሪያ ያለውና ጥልቅ ለም መሬት የሆነ፣
– የአፈር አሲዳማነት፡ ፒ.ኤች 5.5-6.5 አሲዳማ
ብርሃን
-የኩርት ዕድገትና ልምላሜ፡ ረጅም የቀን ክፍለ ጊዜ ከ12 ሰዓታቶች በላይ
ማዳበሪያ
-መደበኛ መጠን፡-በሄክታር N-P-K= 250-77-128ኪግ.
-ካልሺየም ማዳበሪያ፡- በዝቅተኛ የአሲድ መጠን፣ በአፈር ውስጥ የሚገኝ
አልሙኒየም መርዛማ ያደርገዋል፣
-አንዴ የአፈሩ አሲዳማነት ወደ 6.5 ከተስተካከለ ውጤቱ እስከ አራት አመታት ይቆያል፡፡ ማዳበሪያውን በመኸር እና በፀደይ መጀመሪያ ወራት መካከል ማድረግ
-ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያ፡- ከ15-25 ቶን/ሄክታር በየአመቱ ማድረግ
● : መዝራት ○ : ምርት መሰብሰብ
ዘር ማፅዳት : የነጭ ሽንኩርቶችን ዘር በወንፊት ማስቀመጥና በፀረ ተባይ መድሀኒት ድብልቅ ውስጥ ለአንድ ሰዓት ነክሮ ማቆየት፣ ከተነከረ በኋላ ጥላ ስር እንዲደርቅ ማድረግ፡፡
አተካከል፡ ክፍልፋይ ኩርት መጨረሻ ጫፉ ወደ ላይ በማድረግና ስር ያለበትን አካል ወደ አፈር በማድረግ መትከል፣ መሬቱ ከመቀዝቀዙ አንድ ወርቀደም ማለት አለበት፡፡
አገዳ ማስወገድ፡ ወዲያው ማስወገድ፡፡ በጠዋት ጊዜ እና/ወይም በምዕራብ ፀሐይ ስትጠልቅ ምቹ ጊዜ ነው፡፡
ምርት መሰብሰብ፡ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት 65 በመቶ መድረቅ አለበት ስለዚህ 2/3 አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ቅጠሉ ሲደርቅ፣ ከ2-3 ቀናቶች በሜዳ ላይ
እንዲደርቅ ማድረግ፡፡
ማቆያ/ማከማቻ፡ ከታጨደ በኋላ የነጭ ሽንኩርቱን በደንብ አየር በሚያስገባ ጥላ ውስጥ ማንጠልጠል፡፡