የአስተራረስ ሁኔታ


ሙቀት

  • ቡቃያ የመብቀል ሙቀት መጠን: 25ዲሴ
  • ከፍተኛው የእድገት ሙቀት : 15~25ዲሴ
  • የእድገት መዛባት የሙቀት መጠን: ዝቅተኛው 5ዲሴ, ከፍተኛው 35ዲሴ

አፈር

  • ሁሉም የአፈር ዓይነቶች ከአሸዋ እስከ ከባድ አፈር
  • አሸዋ ወይም አሸዋማ አፈር በመጀመሪያ ለሚበቅሉ ሰብሎች ምርጥ ነው ተብሎ ይታሰባል።
  • የሰብል የሸክላ አፈር እና ደቃቅ አፈር ሰብሉ ከበቀለ በኋላ ይመረጣል፡፡ – የአፈር አሲድነት: pH 6.0 ~ 6.8

    የፀሐይብርሃን

    • ለብሮኮሊ በጣም ጥሩው ሁኔታ ሙሉ ፀሐይ ነው።
    • ነገር ግን ብሮኮሊ ከቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሰብል አንዱ ነው፣ የአየር ሁኔታን ማቀዝቀዝ ያስፈልገዋል፣ ብሮኮሊ በቀን ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተወሰኑ ጥላዎችን መቋቋም ይችላል፡፡

    ማዳበሪያ

    • መደበኛ መጠን: N-P-K = 150-100-170 ኪ.ግ / ሄክታር
    • ናይትሮጅን 120 ኪ.ግ፣ 80 ኪ.ግ ፎስፎረስ እና 60 ኪሎ ግራም ፖታሽየም በሚተክሉበት ጊዜ መደረግ አለበት፡፡
    • የቀረው የናይትሮጅን ግማሽ ክፍል ከተተከለ በኋላ በ 30 እና 45 ቀናት ውስጥ በሁለት የተከፈለ መጠን መጠቀም አለበት፡፡

    የአስተራረስ መርሃግብር

    አጠቃላይ አስተራረስ

    በኢትዮጵያ ሰብል ለመዝራት 3 ወቅቶች አሉ፡፡ ●: የችግኝ ጊዜ (ለመብቀል ከ 5 ~ 17 ቀናት)

    ●: ችግኝን መትከል (ከ3-5 ሳምንታት ከቡቃያ በኋላ)

    ●: ምርት መሰብሰብ (ከተተከለ ከ50-75 ቀናት በኋላ)

    * ምርት መሰብሰብ (ከተተከለ ከ50-75 ቀናት በኋላ) ቀጥታ መትከል (በቀጥታ መትከል አይመከርም እና በቀጥታ መትከል ከፈለጉ፣ ችግኝ ከመትከል ከ 2 ~ 3 ሳምንታት በፊት ዘርን መዝራት) የሚፈለገው ዘር: 500 ግ/ሄክታር ዘሮች ያስፈልጋሉ

    የመትከያ ቦታ

    የበለፀገ እና ለም የሆነ አፈር ያስፈልገዋል፣ በብዙ ማዳበሪያዎች የዳበረ። ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ብሮኮሊ ወይም ሌሎች ብሮኮሊ-ዝርያ እፅዋት (ብራሰልስ ቡቃያ፣ ጎመን፣ አበባ ጎመን እና ጥቅል ጎመን) የበቀሉባቸው ቦታዎች ላይ መትከል አይገባም፡፡

    ንቅለ ተከላ

    15 ሴ.ሜ ቁመት ያላቸው ተክሎች ከ5-6 ዋና ቅጠሎች በ40 ሴ.ሜ ርቀት ላይ ይትከሉ፣ በ‘ክለብ ሥር በሽታ’ የተበከለ እርሻ ሬትን አይጠቀሙ።

    ቀጥታ መትከል

    በሄክታር 2 ኪሎ ግራም የሚሆን ዘር ሊያስፈልግ ይችላል። ችግኞቹ እንዲጠነክሩ ከመትከል ከ 4-6 ቀናት በፊት መስኖ መጠቀምን ማቆም ነው (ቀጥታ መትከል አይመከርም እና

    ለመብቀልም በአፈር ሙቀት ላይ የተመሰረተ ነው)፡፡