ምንም እንኳን በቆሎ ለወይና ደጋ እና በቆላ የአየር ፀባይ የሚመረት ሰብል ቢሆንም በምርምር በደጋ አየር ፀባይም ሊመረቱ የሚችሉ የበቆሎ ዝርያዎችን ማግኘት ተችሏል፡፡ በሀገራችን የደጋ በቆሎ ማሻሻያ ምርምር በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ኤእና በ ’ ’ ዓለም አቀፍ የበቆሎና ስንዴ ማሻሻያ ማዕከል በ199ዐ ዓ.ም. በጋራ በአምቦ ዕፅዋት ጥበቃ ምርምር ማዕከል ተቋቋመ፡፡
የደጋ በቆሎ የደጋ ሰብል እንደመሆኑ መጠን ደጋማ የአየር ፀባይ ይስማማዋል፡፡ በመሆኑም ከባህር ጠለል በላይ ከ18ዐዐ እስከ 27ዐዐ ከፍቆ ላይ የሚበቅል ቢሆንም ለጥሩ ምርት ግን ከ18ዐዐ እስከ 25ዐዐ ከፍቆዎች በይበልጥ ይስማሙቆል፡፡
የደጋ በቆሎ እንደ ሌሎቹ የወይና ደጋና የቆላ በቆሎ ዝርያዎች የሚበቅሉበት ለም የሆነና ውሃ የማይቋጥር የአፈር አይነት የሚስማማው ሲሆን በተጨማሪም በደንብ በተንጣፈፈ ኮትቻ አፈር ላይም ይበቅላል፡፡
እስካሁን በተካሄዱት የደጋ በቆሎ ማሻሻያ የምርምር ሥራዎች ሁለት ዝርያዎች ለተጠቃሚው ተለቀው በጥቅም ላይ በመዋል ላይ ናቸው፡፡ ከተለቀቁት ዝርያዎች ውስጥ አንዱ ዲቃላ ( – ) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ዲቃላ ያልሆነ ( ) ነው፡፡
የደጋ በቆሎ በፀዳ ማሳ ላይ እንደ አፈሩ ሁኔቆ ቺና የአረም ዓይነት ከ2 እስከ 3 ጊዜ ጠለቅ ተደርጐ ማሣው መቆረስ አለበት፡፡ ከፍተኛ ዝናብ ባለባቸውና አፈሩ ኮትቻ በሆነበት አካባቢዎች ማሳው ውሃ እንዳይቋጥር በማሳዎቹ ውስጥ የማንጣፈፊያ ቦይዎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
ሠንጠረዥ 1. የተለቀቁ የደጋ በቆሎ ዝርያዎች ባህርያትና የአመራረት ዘዴ ስለዝርያዎቹ አጠቃላይ መረጃ በሠንጠረዥ 1 ላይ ተቀምጧል፡፡
አዘራር
በቆሎ በመስመር ሲዘራ ለአሰራር ከመመቸቱ ባሻገር የሚጠበቀውንም ከፍተኛ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡ ነገር ግን በብተና ከተዘራ ከፍተኛ የምርት ቅነሳ ያስከትላል፡፡ በመስመሮች መካከል 75 ሣ.ሜ እና በዘሮች መካከል ደግሞ 25 ሣ.ሜ በመተው ከ3 እስከ 5 ሣ.ሜ ጥልቀት ላይ ዘርቶ አፈር ማልበስ ያስፈልጋል፡፡ ተዘርተው ያልበቀሉ ዘሮች ካሉ በዘር ወቅት የተረፈ ዘር ካለ ባልበቀሉት ቦቆዎች ላይ ወዲያው መተካት ይቻላል፡፡
የዘር ወቅት
ይህ ወቅት ከቦቆሎ ቦቆ የሚለያይ ቢሆንም ሁሉም አካባቢዎች የአካባቢያቸው ዝናብ እንደጀመረና አፈሩ በቂ እርጥበት
እንዳገኘ ከመጋቢት ወር እስከ ግንቦት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይዘራል፡፡ ውሃ ገብ ወይም የመስኖ ውሃ የሚያገኙ አካባቢዎች ከሆኑ ግን በበጋ ወራትም ዝርያዎቹን ማምረት ይችላሉ፡፡
ምርት መሰብሰብና ማከማቸት
በቆሎን በወቅቱ መሰብሰብና ማከማቸት አላስፈላጊ ከሆኑ የምርት ብክነቶች ይጠብቃል፡፡ በቆሎ የራሱ የሆነ የመድረስ ምልክት ያሳያል፡፡ ይኸውም ቅጠሎቹና ግንዱ ከመድረቃቸው በተጨማሪ የበቆሎ ፍሬዎች ከቆረቆንዳው የሚጣበቁበት ጫፍ ይጠቁራል ( ) ፡፡ በቆሎው ይህ ደረጃ መድረሱ ከተረጋገጠ በኋላ በሳምንት ወይም በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ መሸልቀቅ አለበት፡፡ የተሸለቀቀው በቆሎ ተወሰኑ ቀናት ንፋስ ወይም ፀሃይ እንዲያገኘው ከተደረገ በኋላ ተፈልፍሎ በዕቃ ገብቶ መከማቸት አለበት፡፡
የሰብል ጥበቃ
አረም
በቆሎ በተፈጥሮ የአረምን ጥቃት የሚቋቋምበትና የአረም ጥቃትን መቋቋም የሚያቅትበት የዕድገት ደረጃ አለው፡፡
በቆሎው ተዘርቶ ከበቀለ በኋላ በመጀመሪያዎቹ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ ከአረሞች ጋር የመፎካከር አቅም የለውም፡፡
እንደዚሁም በቆሎ ከሠው ጉልበት በላይ ማለፍ ሲጀምር ከአረሞች ጋር የመፎካከር አቅም እያዳበረ ይሄዳል፡፡
በመሆኑም በቆሎ ከተዘራበት ቀን ጀምሮ ከ3ዐኛ ቀን እስከ 5ዐኛው ቀን ላሉት ተከታታይ 18 ቀናት ውስጥ ማሳው
ከአረም ንጹህ ካልሆነ ከፍተኛ የምርት ቅነሳ ያስከትላል፡፡
በሽታ
የደጋ በቆሎ ዝርያዎች በደጋማው የአየር ፀባይ ውስጥ የተለመዱትን የበቆሎ ቅጠል አድርቅ በሽቆዎችን (ለምሳሌ ፡- እና ) የሚቋቋሙ ቢሆኑም በተለምዶአዊ ዘዴ የበቆሎ በሽቆዎችን የመከላከል መፍትሔዎችን በተጨማሪ መጠቀም ውጤቆማ ያደርጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በቆሎውን ከሌሎች ሰብሎች ( ) ጋር አሰባጥሮ መዝራት፣ ከሌሎች ሰብሎች ጋር በፈረቃ መዝራት ከኑግ ጋር እንዲሁም ዘር ከመዝራት በፊት ማሣ የማጽዳት ሥራ መሥራት የቺነዚህን በሽቆዎች ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡፡
ተባይ
በቆሎ ማሣ ላይ እንዳለ የበቆሎ አገዳ ቆርቁር ትል ( ) እና ከተሰበሰበ በኋላ ደግሞ የጐተራ ተባዮች ነቀዞች ከፍተኛ ጉዳት ከሚያደርሱት ተባዮች ውስጥ ዋንኛዎቹ ናቸው፡፡ በተለይ በደጋ አካባቢዎች የተለመደው በቆሎን የመዳረሻ ጊዜው ሳይደርስ ከነ አገዳው ሰብስቦ አንድ ቦቆ ላይ መከመር የአገዳ ቆርቁር ትልን በከፍተኛ ደረጃ እንዲራባና ጉዳት እንዲያደርስ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ድርጊት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ወቅትን ጠብቆ መዝራትና ከሌሎች ሰብሎች ጋር በማሰባጠርና በማፈራረቅ በቆሎን መዝራት የዚህን ትል ጉዳት ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ምናልባት የግንደ ቆርቁር ትል ወረርሽኝ በአካባቢው የሚቆወቅ ሆኖ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ እንደ እና የተባሉ ፀረ-ተባይ ሚካሎችን በትክክለኛው መጠን በቆሎ ከበቀለ በኋላ ጉልበት አካባቢ ሲደርስ መጠቀም ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የጐተራ ተባዮችን ለመከላከል በቆሎን በወቅቱ ሰብስቦ ለተወሰኑ ቀናት ፀሀይ በማስመቆት በደንብ መድረቁን አረጋግጦ ቀዝቃዛ የማከማቻ ቦቆ ላይ ማስቀመጥ ጥሩ ነው፡፡ ቢቻል ከጤፍ ዘር ጋር ቀላቅሎ ማስቀመጥ ደግሞ የበለጠ ጥሩ ነው፡፡ 2% እና 5% ዱቄቶች በቆሎን አሽቶ ማስቀመጥ እንደ መጨረሻ አማራጭ ተደርጐ ሊወሰድ ይቻላል፡፡