2–1. የዶሮ እርባታ ዘዴዎች
የዶሮ እርባታ በገጠር ላለው ማህበረሰብ ባህላዊ፣ ሕብረተሰባዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦው ላቅ ያለ ነው። በተለምዶው ዶሮ እርባታ በሴቶች፣ በሕጻናት፣ በአካል ጉዳተኞች እንዲሁም በአዛውንቶች የሚከናወን ሲሆን የዕለ ት ጉርሳቸውን እንዲያሟሉ እና ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ አቅም ይሆናቸዋል
። በአሁን ወቅት ዶሮ እርባታ ለብዙዎች መደበኛ ሥራ እና የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።
በኢትዮጵያ ሦስት አይነት የዶሮ እርባታ ዘዴዎች በመተግበር ላይ አሉ። እነዚህም መንደርን መሰረት ያደረጉ እርባታዎች፣ በከፊል የተደራጁ የዶ ሮ እርባታ ዘዴዎች ፣ እና ሙሉ በሙሉ የተደራጁ/ዘመናዊ የእርባታ አ ሰራር/ ናቸው።