መግቢያ


ጤፍ ሀገር በቀል ከሆኑት የብርዕ እህሎች አንዱና ዋነኛው ሲሆን በበርካታ  የአገሪቱ ክፍሎችም በሰፊው ይመረታል፡፡ በአማካይ በዓመት ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ጤፍን ለማምረት ይውላል፡፡ ጤፍ በዋናነት ለእንጀራ ያገለግላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሰብሉ የሚገኘው ጭድ ለከብት ምግብና ከጭቃ ጋር ተቦክቶ ለቤት መምረጊያነት ያለግላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ውጪ ከጤንነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ከብርዕና አገዳ ሰብሎች መካከል በከፍተኛ መጠን ወደ ውጭ እየተላከ ይገኛል፡፡ ጤፍ ግሉትን የተባለው ፕሮቲን ስለሌለው ለዚህ ፕሮቲን አለርጂክ የሆኑ ሰዎች ጤፍን መመገብ እንደ አማራጭ ይወስዳሉ፡፡