ሙቀት


ሙቀትን መቆጣጠር

ሙቀትን መቆጣጠር ምርትማ የሆነ የዶሮ እርባታ ለማካሄድ ወሳኝ ነገር ነ  ው። የሙቀት ቁጥጥር ለዶሮዎቹ እንደየዕድሜአቸው የሚደረግ ይሆናል።  በአፍላ ወቅት (ከ1  እስከ 4 ሳምንት) ላሉ ጫጩቶች ከፍ ያለ ሙቀት የሚ  ፈልግ ይሆናል። ለንግድ በተቋቋሙ የዶሮ እርባታ ተቋሞች ይህ ሙቀት ሰ  ው ሰራሽ በሆኑ መንገዶች የሚደረግ ይሆናል። ይህም በኢንፍራ ሬድ አሞ  ፖሎች፣ መከለያ መፈልፈያዎች፣ እና የማሳደጊያ ሳጥኖች ውስጥ በማኖር  የሚቻል ይሆናል። በተጨማሪም ጫጩቶቹ ከመፈልፈያዎቹ ርቀው እንዳ  ይሄዱ ጠባቂ ያስፈልጋቸዋል። ይህም ርቀው ሲሄዱ ከሚያጋጥማቸው  ይጠብቃቸዋል። መፈልፈያዎች ለእያንዳንዱ የጫጩት ጀማ የታጠቡ እና  የበሽታ ማጥፊያ የተረጨባቸው እንዲሆኑ ያስፈልጋል።

lመፈልፈያዎቹም ጠርዛቸው ስል ሳይሆን ዱልዱም እና ክብ መሆን አለ  በት። ይህም ጫጩቶቹ በሚተራመሱበት ሰዓት እንዳይጎዱ ያደረጋቸዋል።

lለጫጩት በሚሆን አስፈላጊ መሳሪያ የተሰራ መሆን አለበት።

lየማይታጠብ ከሆነ የሚጣል መሆን አለባቸው።

በአግባቡ ታቅዶ የተዘጋጀ የዶሮዎች መከለያ ያለው ማሞቂያ

በቤቱ ውስጥ ያለው ማሞቂያ ችግር ካጋጠመው ጫጩቶቹ ለየት ያለ ባህርይ  ማሳየት ይጀምራሉ። ለምሳሌ ሙቀት መጠኑ ከመደበኛ ወረድ ያለ ከሆነ  ጫጩቶቹ ማሞቂያው ዙሪያ መከማቸት ይጀምራሉ። ሙቀት መጠኑ ደግሞ  ከፍ ካለ ጫጩቶቹ ተበታትነው ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ማለክለክ፣ ክንፋቸውን  መክፈት እና ምግብ መመገብ ይቀንሳሉ።