ምርት መሰብሰብና ማከማቸት


አኩሪ አተር ቅጠሉ ከአረንጓዴነት ወደ ቢጫነት ሲቀየርና ደርቆ መራገፍ ሲጀምር መታጨድ አለበት፡፡ በጣም እስኪደርቅ መጠበቅ የለበትም፡፡ ምርቱ በአፈርና ሌሎች ቆሻሻዎች እንዳይበከል በንፁህ አውድማ ላይ መወቃት አለበት፡፡ ከተወቃም በኋላ የእርጥበት መጠን ከ 10-13 ሲሆን ጥሩ የአየር ዝዉዉር ባለበት ጎተራ መከማቸት አለበት፡፡