ሰብል ጥበቃ


አረም

የፈረንጅ ሱፍ ማሳ በተለያዩ ዓመታዊ ፣ ቋሚ  እና ጥገኛ አረሞች እንዳይጠቃ በመጀመሪያዎቹ ሁለት እና ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከአረም ነፃ መሆን አለበት፡፡ የሰብሉ እደገት በቡቃያነቱ ዘገምተኛ ስለሆነ በቀላሉ ሊጠቃ ይችላል፡፡ ተክሉ 50 ሳ.ሜ  ከመሬት ከፍ ካለ በኋላ ግን በሰፋፊ ቅጠሉ መሬቱን ስለሚሸፍን አረሙን በቀላሉ ሊቆጣጠር ይችላል፡፡

በሽታ

የፈረንጅ ሱፍን ከሚያጠቁ  በሽታዎች መካከል በቅጠሉ ላይ  ጠቃጠቆ የሚፈጥሩ አልተርናሪያ እና ሴፕቶሪያ (Aleternaria and septoria) የሚባሉት ይገኙበታል፣ በጣም አደገኛ የሆነው በሽታ ግን ስኬሎሮሺያ (  Selerotinia ) ነው፡፡ የመንግስት እርሻዎችን ተስፋ ሊያጨልም የቻለው እና ሰብሉን ከምርት ውጭ ያደረገው ይኽው በሽታ ነው፡፡ በአገራችን የሰብሉ አምራቾች በሽታውን ለመከላከል፤-

  • ከበሽታው ነፃ የሆነ ዘር መጠቀም፣
  • ሰብሉን በፈረቃ መዝራት እና
  • የሰብሉን ቅሪቶች ማሳ ውስጥ እንዳይቀበሩ መጠንቀቅ ወይም በደንብ ለፀሐይ እንዲጋለጡ ማድረግ ናቸው፡፡

ተባይ

የፈረንጅ ሱፍን ከሚያጠቁት ተባዮች ውስጥ የአሜሪካ የጓይ ትል /Heliothis armigera/  እና ምስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ ተባዮቹ የሰብሉን ስርና ግንድ በመብላት በሰብሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህንም ተባዮች ለመቆጣጠር የተባዮቹን ጥቃት የሚቋቋሙ ዝርያዎችን ወይም ተስማሚ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችን ከባለሙያ ምከር ጋር መጠቀም ያስፈልጋል፡፡