የነጭ ሽንኩርት አዥጎርጉር ቫይረስ
– በቅጠሎች ላይ ቢጫና አረንጓዴ ዥጉርጉር ንድፍ ይፈጥራል፣
-በክሽክሽ እና በአይን በማይታዩ(ቅንቅን) አማካኝነት የሚተላለፍ ነው፣
-እንደ አሴሪያ ቱሊፔ ሁኔታ፣ በክረምት ወደ ኩርት ይተላለፋል፡፡ ከዛም የአየር ሙቀቱ ከ20ዲሴ በላይ ሲሆን በሽታው ይነሳል፣
-በጣም ከባዱ ችግር በኩርት የሚመጣ መበከል ነው፡፡ ምክንያቱም ነጭ ሽንኩርት ዘር የሚፈላው(የሚራባው) በኩርት አማካኝነት ስለሆነ ነው፡፡
የመቆጣጠር ዘዴ
-በመጀመሪያ እንዳይከሰት ትኩረት መስጠት ምክንያቱም አንዴ ከተበከለ ለመፈወስ አስቸጋሪ ነው፣
-ከቫይረስ የፀዱ ክፍልፋይ ኩርት መምረጥ ወይም በሽታ የሚቋቋም ዝርያ መምረጥ፣
-ጤናማ የነጭ ሽንኩርት ዘር መምረጥ፣
-ክሽክሽና ቅንቅን ቫይረስ እንዳያስስተላልፉ መከላከል፡፡
-በዝናብና በመስኖ ምክንያት በሚፈጠር ከባድ እርጥበት ሁኔታ ውስጥ ይከሰታል፣
-ትንሽ ግራጫማ ነጠብጣብ በቅጠሉ ላይ ይታያል በኋላም ወደ ቡኒነት ይቀየራል፣ በመጨረሻም ጥቁር ሸጋታዎች በነጠብጣቦቹ ላይ በወፍራሙ ይከሰታሉ፡፡
-ዘሮችን ማፅዳት እና የተበከሉትን ተክሎች ማስወገድ፣
-ከአሊየም ተክሎች በስተቀር በየ2-3 ዓመታቶች ውስጥ ሰብሎችን መቀየር፣
-ምርት ከመሰብሰባችን በፊት ከ7-14 ቀናቶች በፊት ባሉት 10 ቀናቶች ውስጥ ከ3-5 ጊዜ ኬሚካል መርጨት፣
-ኬሚካሎች፡- ዳኮኒል (ክሎሮታሎኒል 75%) ፣ ፕሮፒ(ፕሮፒኔብ 70%)፣ ኢፕሮ(ኢፕሮዳይኦን 50%)፣ ዲቲአኖን(ዲቲአኖን 55%) የሚበጠበጡ ዱቄት፡፡
ስርና ኩርት አበስባሺ (ሁዋይት ሩት)
-በአፈር ላይ የሚገኝ አፈር ወለድ በሽታ ነው፣
-ለስላሳ ነጭ ዘንገፈንገስ በኩርት ውጭኛው ቆዳ ላይ ይከሰታል፣ በመጨረሻም ጠቅላላ ራስ ሽንኩርት ወደ ጥቁርነት ይቀየርና ይበሰብሳል፣
-ትይዩ ባሉ ቅጠሎች ላይ መገርጣት ይጀምራል፣ በኋላም በጠቅላላ ቅጠሎቹ ወደ ቡኒነት ይቀየሩና ይደርቃሉ፡፡
የመቆጣጠር ዘዴ
-እንዳይከሰት ትኩረት መስጠት ምክንያቱም አንዴ ከተበከለ ለመፈወስ
አስቸጋሪ ነው፣
-ከአሊየም ተክሎች በስተቀር በየ3-4 ዓመታቶች ሰብሎችን መቀየር፣
-ዘር ማፅዳት፡- ዘሮችን በቤኖራም የሚበጠበጡ ዱቄት መንከር(ቤኖማይል 20% + ቲራም 20%) 4ግራም ዱቄት ለ 1ኪግ ዘር፣
-አፈር ማፅዳት፡- ዘር ከመዝራታችን በፊት ባሉት ከ2-3 ቀናት አፈሩን በዳዞሜት ደቃቅ ማጠንና በፕላስቲክ መሸፈን፣
-በምንዘራበት ወቅት፡- ከመዝራታችን በፊት እና/ወይም ከዘራን በኋላ የቲቡኮናዞል 25% ውህድ በሄክታር 1000ሊትር መርጨት፡፡
የሽንኩርት ስርና ኩርት ትል (ኦኒየን ማጎት)
-እጩ ስሩን እና/ወይም ኩርትን ይጎዳል፡፡ ቅጠሎቹ ወደ ቢጫነት ይቀየሩና
ይደርቃሉ፣
-በአመት ሶስት ጊዜ ይከሰታሉ፡፡ በከፍተኛ የሚከሰቱበት ወቅትም ሚያዝያ፣ሰኔና ጥቅምት ላይ ነው፡፡
-ያልበሰለ ወይም ያልደረሰ ፍግ አለመጠቀም፣
-መስኩን ስናዘጋጅ ወይም በመጋቢት የመጀመሪያ ወቅት ላይ ካርበን ደቃቅ (ካርቦፉራን 3%) በሄክታር 50 ኪግ መርጨት፣ -ከልክ በላይ ንዳይከሰት ለመከላከል በመጋቢት መባቻ ላይ ከ7-10 ባሉት ቀናቶች ውስጥ ከ1-2ጊዜ ፀረ ተባይ መርጨት፣-በሽታው ከተከሰተ በኋላ ከ1500-2000 ተዛማችነት ያላቸው ፀረ ተባይ በማዋሀድ መርጨት፡፡
-አንድ ላይ በቡድን በመሰባሰብ የስሩን ጫፍ ይጎዱታል፣ ስሮቹ ይበጣጠሳሉ ኩርትም ይበሰብሳል፣
-በማከማቻ ወቅት በከፍተኛ የአየር ሙቀትና በርጥበት ሁኔታ ውስጥ ይባዛሉ፡፡
-ምርት ከሰበሰብን በኋላ ባሉት ከ4-5 ቀናቶች ውስጥ ተክሉን በፎስቶክሲን(አልሙኒየም ፎስፌድ 56%) ተክሎቹን ማጠን፣
-ዘር ማፅዳት፡- ክፍልፋይ ኩርትን 1000 ተዛማችነት ያላቸው ውህድ ውስጥ ዳይሜቶ(ዳይሜቶኤት 46%) ከ30-60 ደቂቃዎች መዘፍዘፍ፣
-አፈር ማፅዳት፡- የፎሬት ደቃቅ(ፎሬት 2%) መርጨትና መስኩን ማረስ፣ በሄክታር 80ኪግ የፎሬት ደቃቅ፣
-የንቅለተከላውን ላስቲክ ማንሳትና ዳይሜቶ ውህድ(ዳይሜቶኤት 46%) ከ2-3 ጊዜ መርጨት፣ በሄክታር 10000 ሊትር፡፡
ተህዋስያን(ብሎት ኔማቶድ)
-እጭና ከእጭነት ያለፈው ተህዋስያን በኩርትና በቅጠሎች መሀል ይገቡና ፈሳሹን የሽንኩርት ክፍል ይመጡታል፣
-በማከማቻ ወቅት በከፍተኛ የአየር ሙቀትና በእርጥበት ሁኔታ ውስጥ ይባዛሉ፡፡ እናም በክምችት ወቅትም ውድመትን ያመጣሉ፣
-የሽንኩርት ንጥረነገር ይዘት ላይ እጥረትን ይከስታሉ፡፡ ሽንኩርት ራሱም እንዲበሰብስ ያደርጋሉ፣-የተክሉ ዕድገት ጥሩ አይሆንም፣ የቅጠሉ ጫፍ ገና በለጋው ይጠቀለልና ይደርቃል፡፡
የመቆጣጠር ዘዴ
-ዘር ማፅዳት፡ ክፍልፋይ ኩርትን 1000 ተዛማችነት ያላቸው ውህድ ውስጥ ዳይሜቶ(ዳይሜቶኤት 46%) ውስጥ በማድረግ መዘፍዘፍ፣
-አፈር ማፅዳት፡ ክፍልፋይ ኩርት ስንተክል የኢቶፕ ደቃቅ (ኢቶፕሮፎሰ 5%) በሄክታር ከ100-120ኪግ ደቃቅ መርጨት፡፡