ተስማሚ አካባቢዎች


በተፈጥሮ ወይም በወፍ ዘራሽ ዘዴ በተለያዩ የአፈር አይነቶችና ከፍታዎች ላይ  ይበቅላል፡፡ ሆኖም ጉሎ ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ከፍታና ውሃ የማይቋጥር አሸዋማ አፈር ( sandy loam ) በጣም ይስማማዋል፡፡ ውሃ የሚቋጥር፣ የሸክላ ወይም ጨዋማ አፈር በፍፁም  አይስማሙትም፡፡

ስሩ በጣም ጥልቅና ዕድገቱም በጣም ፈጣን በመሆኑ የእርጥበትን አጥረት በፅኑ ይቋቋማል፡፡ ስለሆነም ጉሎ በዝናብ አጠር አካባቢዎች በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ ሰብሉ ከፍተኛ ምርት እንዲሰጥ  እስከ 400 ሚሊ ሜትር የዝናብ መጠን በእድገቱ ወቅት ይፈልጋል፡፡