ተስማሚ አካባቢ


ቲማቲም ሞቃት የአየር ንብረት ይፈልጋል፡፡ ከፍተኛው ሙቀት ከ23-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሙቀቱ ከዚህ ከበለጠ ወይም በጣም ከቀዘቀዘ  የተክሉን ዕድገት በመግታት፣ አበባውን በማራገፍና ፍሬውን በማሳሳት ምርቱን ይቀንሰዋል፡፡ ዝናብ ወይም እርጥበት ከጨመረ ደግሞ ተክሉ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃል፡፡ በአጠቃላይ ከዝናብ ነፃ የሆነ፣ መካከለኛ ሙቀት እና ከአራት እስከ አምስት ወራት ያለው ወቅት ቲማቲም ለማምረት ይመረጣል፡፡ ቲማቲም ረጅም ሥር ስላለው ቀላል፣ ለምና ውሃ የማይቋጥር አፈር አስተማማኝና ጥራት ያለው ምርት ለማግኘት ይረዳል፡፡ የአፈሩ ኮምጣጣነት ከ 6.5-7.5 ሆኖ የንጥረ ነገሩ ይዘቱም የተመጣጠነ ቢሆን ይመረጣል፡፡