ተከላ


የፓፓያ ተክል የ5ዐ ሳ.ሜ. ጥልቀትና ስፋት ያላቸው ጉድጓዶች ከ2 እስከ 3 ሜትር እንደየተክሉ ቁመት ማለትም ለአጫጭሮቹ በማቀራረብ ለረጃጅሞቹ በማራራቅ ጉድጓዶች ይቆፈራሉ፡፡ በተክሎችና በመስመሮች መካከል የሚኖረው ርቀት እንደዝርያው፣ እንደማምረቻው ቦታና ፺ንደ አምራቹ የአመራረት ዘዴ ይለያያል፡፡ የላይኛው አፈር ከ2 ባልዲ ፍግ ከተገኘም ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ግማሽ ኪሎ ግራም ዳፕና ግማሽ ኪለ ግራም ዩሪያ ጋር በመደባለቅ ወደ ጉዳጓዱ ይመለስና እንዲብላላና አፈሩ ቦታውን እንዲይዝ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወራት ይተዋል፡፡ ቦታው እንዳያሳስት ምልክት ይደረጋል፡፡ የመስኖ ውሀ  ካለ በማንኛውም ጊዜ ሊካሄድ ቢቻልም የዝናብ መጀመሪያ ወቅት በጣም ተስማሚ ነው፡፡

ችግኞች በሚተከሉበት ወቅት ልፍስፍስ እንዳይሆኑ በመጨረሻው ሳምንት የው፺  አሰጣጡን በመቀነስ ለተከላ ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ በፕላስቲክ ከረጢት ላይ የተመረቱ ችግኞች ቁመት 2ዐ ሳ.ሜ. የግንድ ውፍረቱ ደግሞ የእርሳስ ውፍረት ያክል ወደ ቋሚ ማሳ ይዘዋወራሉ፡፡

በተከላ ወቅት ችግኙ በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ በነበረበት ሁኔታ  ሊቀመጥ ይገባል፡፡ በፕላስቲክ ውስጥ ከነበረበት ጥልቀት ጨምሮ ወይም ቀንሶ መትከሉ በተክሉ ዕድገት ላይ ችግር ያስከትላል፡፡ በተከላ ወቅት በችግኙ ዙሪያ ያለውን አፈር መጠቅጠቅና የአፈሩ ዕርጥበት አናሳ ከሆነ ውሃ  ማጠጣት የተክሉ ሥር ከአፈሩ ጋር እንዲያያዝና እድገቱ ፈጥኖ እንዲቀጥል ይረዳል፡፡