አጠቃላይ ንድፍ
ችግኝ ማፍላት :
ቲማቲም በመደበኛነት በችግኝ ማፍያ በማፍላትና ተክሉን በማጓዝ እንተክለዋለን ምክንያቱም ችግኝ በማፍላት ስንተክል የተሻለ ውጤት ይሰጠናል፡፡
በጥቁር ፕላስቲክ መሸፈን(ትነተክል):
ተክሉን አጉዘን ከመትከላች በፊት መሬቱን በጥቁር ላስቲክ መሸፈን፣ ተክሉ በተሻለ ሁኔታ እንዲያድግ ይረዳል፡፡
ተክል ማጓዝ (ንቀለ ተከላ):
ችግኞቹ ሙሉ በሙሉ ሲያድጉ ቦታ ቀይሮ(አጓጉዞ) መትከል ያስፈልጋቸዋል፡፡ የአየር ጠባዩን ማየት፣ ከሰዓትና ደመናማ ቀን ችግኙን አጉዞ ለመትከል ጥሩ ነው፡፡
መከርከም:
ቀደም ብለው የነበሩ ቅርንጫፎችን ማስወገድ ሌሎች አዲስ ቅርንጫፎች እንዲበቅሉ ይረዳል፡፡
መቸከል :
የቲማቲም ተክል ለእድገቱና ለክብደቱ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ችካል ያስፈልገዋል፡፡
ምርት መሰብሰብ :
ከተተከለ ከ75-90 ቀናቶች በኋላ የቲማቲም ምርት መሰብሰብ ይቻላል፡፡ በአብዛኛው የቲማቲም ተክል ፍሬ ደርሰው ሲበስሉና ወደ ቀይነት ሲቀየሩ በእጅ ይሰበሰባሉ፡፡