ችግኝ ማፍላት:- ከመተከሉ በፊት ከ40-45 ቀናት ችግኝ ማፍላት፡፡ በእያንዳንዱ ቀዳዳ በ1/4ኛ ኢንች ጥልቀት የበርበሬ ዘሩን በመትከያ ሳጥን መዝራት፡፡
ችግኝ ማፍያ መደብ:- ችግኞቹን እስከ 60 ቀናት እንዲያድጉ ማድረግ፡፡ ዋናው ቅጠል ከ2-4 ቅጠሎች ሲያድጉ ወደ 24 ወይም 36 ክፍል ያለው መትከያ ሰሀን (ሳጥን) አጓጉዞ መትከል፡፡
ተክል ማጓጓዝ:- የሙቀት መጠኑንና የአየር ሁኔታን መፈተሽ፡፡ ከ18°ሴ በታች ለ5 ቀናት መቸከል፡፡ ከተከላ ማጓዝ በኋላ ስር በደንብ እንዲያወጣ በበቂ ሁኔታ ውሃ ማጠጣት፡፡
መከርከም:- የዋናው ግንድ ቅጠልን አየር በተክሉ ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲዘዋወር መከርከም፡፡ የላይኛው ግንድ ቅጠሎችን ለጥላ ስለሚሆኑ በአግባቡ መንከባከብ፡፡
መቸከል:- የበርበሬ ተክል በችካል እንዲቆም ማድረግ የተክሉን ዕድገትና ክብደት ለመደገፍ ይረዳል፡፡
ምርት መሰብሰብ:- በርበሬ ከተተከለበት ከ75-90 ቀናቶች ባለው ጊዜ ውስጥ ምርቱ ለመሰብሰብ ይደርሳል፡፡ ተክሉ ሲበስልና ወደ ቀይነት ሲቀየር እንደ ሁልጊዜው በእጅ ይሰበሰባል፡፡